በአዲስ አበባ ከተማ ምክር ቤት 5ኛ ዓመት የሥራ ዘመን 2ኛ መደበኛ ጉባኤ ከንቲባ አዳነች አቤቤ ለምክር ቤት አባላት ባለፉት 6 ወራት በከተማው በተሰሩ በርካታ ስራዎች ፤ እየተሰሩ ባሉ እና ቀጣይ የሚሰሩ ዘርፈ ብዙ ስራዎች ላይ የሰጣቸው ማብራሪያዎች፡፡
የመሬት ልማት እና አስተዳደርን በተመለከተ፡-
የኦንላይን አገልግሎትን ለማሳለጥ ባለፉት ስድስት ወራት በተሻሻለው ሲስተም 10,528 ካርታዎች ታትመው ተሰራጭተዋል፡፡
የለማ መሬት ዝግጅትና ማስተላለፍ ሥርዓትን ከማሻሻል አንፃር ለተለያዩ አገልግሎቶች 341 ሄክታር መሬት ለማዘጋጀት ታቅዶ 465 ሄ/ር መሬት ማዘጋጀት ተችሏል፡፡
ለተለያዩ አገልግሎቶች የሚውል የከተማዋን ፍላጎት መሠረት ያደረገ 294 ሄክታር መሬት ለማስተላለፍ ታቅዶ 483 ሄ/ር ማስተላለፍ ተችሏል፡፡
የቅድመ ማልማት ጥያቄ ላቀረቡ 54 ባለይዞታዎች በይዞታቸው ላይ ማልማት እንዲችሉ ውሳኔ ተሰጥቷል፡፡
በግማሽ ዓመቱ ለልማት ተነሺዎች 7.4 ቢሊዮን ብር በላይ ካሣ መክፈል የተቻለ ሲሆን ከዚህ ውስጥ በልማት ምክንያት ለተነሱት ልማት ተነሺዎቻችን ለመሠረተ ልማት ዝርጋታ (ለመብራት) አገልግሎት ከ 400 ሚሊዮን ብር በላይ ከፍያ ተፈጽማል፡፡
የአርሶ አደር መብት ፈጠራ አፈፃፀምን በሚመለከት 6,122 ካርታዎች የታተሙ ሲሆን እስካሁን ድረስ 10,873 ካርታዎች ታትመው አርሶ አደሩ እጅ እንዲደርሱ ተደርጓል፡፡
ለ50 አርሶ አደሮች በይዞታቸዉ ላይ እንዲያለሙ ዉሳኔ ተሰጥቶ ወደ ልማት እንዲገቡ ማድረግ ተችሏል፡፡
ባለፉት ስድስት ወራት 41,454 ይዞታዎች ለመመዝገብ ዕቅድ ተይዞ 34,802 ማከናወን ተችሏል፡፡ እንዲሁም ለሚቀርቡ የመብት ምዝገባና የመስክ አገልግሎት ጥያቄዎች ለ84,996 ተገልጋዮች ምላሽ ለመስጠት ታቅዶ ለ94,927 በላይ ማሳካት ተችሏል፡፡
ለ7,310 ተገልጋዮች አዲስ እና አዝ ቢዊልት የግንባታ ፈቃድ ለመስጠት ታቅዶ ለ7,150 ገንቢዎች ፈቃድ ተሰጥቷል፡፡
ለ1,990 ተገልጋዮች የግንባታ ማሻሻያ፤ ማራዘሚያ እና ማፍረሻ ፈቃድ ለመስጠት ታቅዶ ለ2,477 ገንቢዎች ፈቃድ መስጠት ተችሏል፡፡
ለ12,634 ተገልጋዮች የእድሳት እና ጊዜያዊ የግንባታ ፈቃድ ፣ ለ13,451 ገንቢዎች ፈቃድ በመስጠት በርካታ ሕንፃዎች ታድሰዋል፡፡
ባለፉት 6 ወራት በኢንቨስትመንት በተመለከተ
የኢንቨስትመንት እንቅስቃሴ
የኢንቨስትመንት ፍቃድ አሰጣጥ ከታቀደው በላይ አፈጻጸም አሳይቷል፦
አዲስ ፈቃድ፦ 1,750 ታቅዶ ለ 2,549 ባለሀብቶች ፈቃድ ተሰጥቷል።
ማስፋፊያ፦ ማስፋፊያ ፈቃድ 140 ታቅዶ ለ 162 ተሰጥቷል።
ዕድሳት፦ ለ981 የኢንቨስትመንት ፈቃዶች እድሳት ተደርጓል።
የውጭ ዜጎች የስራ ፈቃድ፦ ለ42 የውጭ ዜጎች የስራ ፈቃድ ተሰጥቷል።
ከንቲባ አዳነች አቤቤ
ለተጨማሪ የመረጃ አማራጮች
https://linktr.ee/addisababacommunication
Comments
ምንም አልተገኘም.
አስተያየቶችዎን ይተዉት.