የህዝብ ሀብት በሆነ ትራንስፎርመር ላይ የተቃጣ...

image description
- ውስጥ Current Affairs    0

የህዝብ ሀብት በሆነ ትራንስፎርመር ላይ የተቃጣ ዘረፋ በፀጥታ ኃይሎች ከፍተኛ ክትትልና ጥረት ከሸፈ።

በአቃቂ ቃሊቲ ክ/ከተማ አስተዳደር ለህዝብ አገልግሎት እየተዘረጋ ያለ ትራንስፎርመር ዘርፈዉ ለመሰወር ያደረጉት ሙከራ በፀጥታ ኃይሎች ትልቅ ክትትልና ጥረት በቁጥጥር ስር መዋሉ ተገለፀ።

ድርጊቱ የተፈፀመዉ በክ/ከተማዉ ወረዳ 13 ልዩ ቦታዉ ሀይዌይ አካባቢ ከለሊቱ 8 ሰዓት ሲሆን ዘራፊዎች በተደራጀ ሁኔታ መኪና በመያዝ አዲስ እየተዘረጋ ያለ ትራንስፎርመር ሰርቀዉ ለመሰወር ሲሞክሩ በፀጥታ አካላት ከፍተኛ ጥረት ዘራፊዎቹ ለዲርጊቱ የተጠቀሙበትን ተሽከርካሪ በቁጥጥር ስር በማዋል ትራንስፎርመሩን ማዳን የተቻለ ሲሆን ስርቆት የፈፀሙ ግለሰቦችን በህግ ጥላ ስር ለማዋል ክትትል እየተደረገ ይገኛል።

ለመሰረተ ልማት የተዘረጉ የህዝብ መገልገያ ንብረቶችን የሚዘርፉ እና ጉዳት የሚያደርሱ ግለሰቦችም ሆኑ ቡድኖች ከህግ አይን ሊሰወሩ እንደማይችሉ እና የፀጥታ ኃይሉ ከህብረተሰቡ ጋር በመቀናጀት ተገቢዉን ህጋዊ እርምጃ እንደሚወስድ አሳዉቋል።


Comments

ምንም አልተገኘም.

አስተያየቶችዎን ይተዉት.