የአዲስ አበባ ከተማ ምክር ቤት 5ኛ ዓመት የስራ...

image description
- ውስጥ Current Affairs    0

የአዲስ አበባ ከተማ ምክር ቤት 5ኛ ዓመት የስራ ዘመን 2ኛ መደበኛ ጉባዔ ላይ ትኩረት የተደረገባቸዉ ስራዎች እና የቀጣይ ትኩረት አቅጣጫዎችን በዝርዝር ቀርቧል::

ባለፉት ስድስት ወራት የተመዘገቡ ስኬቶች በጋራ የተደረጉ ጥረቶች እና  የነዋሪዎቻችን ንቁ ተሳትፎ መሆኑን የጠቀሱት ከንቲባ አዳነች አቤቤ የቀጣይ የትኩረት አቅጣጫዎችን አስቀምጠዋል::

👉የኑሮ ውድነትን በዘላቂነት መፍታት
👉የትራንስፖርት አቅርቦት ማነቆዎችን ማስወገድ
👉የውሀ አቅርቦት እና የቤት ልማት ስራዎችን ማፋጠን
👉የአገልግሎት አሰጣጥን ማሻሻል
👉የተጀመረውን የመሶብ የአንድ ማዕከል ዲጂታል የመንግስት አገልግሎት ማእከላትን ማስፋት
👉በተቋማት መካከል ያለውን የአፈፃፀም ልዩነት ማቀራረብ
👉ለህዝብ አገልግሎት የለሙ ቦታዎችን ለታለመላቸው አላማ ብቻ እንዲውሉ ማስቻል 
👉የመልካም አስተዳደር ችግሮችን በቁርጠኝነት ለመፍታትና የነዋሪዎቻችንን ሁለንተናዊ ተጠቃሚነት ለማረጋገጥ በቀጣይ ትኩረት የምንሰጥባቸው ጉዳዮች መሆናቸዉን የአዲስ አባ ከተማ አስተዳደር ከንቲባ አዳነች አቤቤ ለምክር አባላት አሳስበዋል፡፡


Comments

ምንም አልተገኘም.

አስተያየቶችዎን ይተዉት.