የአዲስ አበባ ፖሊስ ጠቅላይ መምሪያ የተሽከርካሪ...

image description
- ውስጥ Current Affairs    0

የአዲስ አበባ ፖሊስ ጠቅላይ መምሪያ የተሽከርካሪ ፍሰቱን ለማሳለጥና ከእንግዶች አቀባበል ጋር በተያያዘ የትራፊክ መጨናነቅ እንዳይፈጠር ዝግ የሚደረጉ መንገዶችን አስታወቀ።

አዲስ አበባ፤ የካቲት 04 ቀን 2018 ዓ/ም (አዲስ ፖሊስ)፡- የጸጥታና ደህንነት የጋራ ግብረ ኃይል 39ኛውን የአፍሪካ ህብረት የመሪዎች ጉባኤ አስመልክቶ አጠቃላይ የጸጥታ ዝግጅቱን አጠናቆ ወደ ስራ መግባቱ የሚታወቅ ሲሆን የተሽከርካሪ ፍሰቱን ለማሳለጥና ከእንግዶች አቀባበል ጋር በተያያዘ የትራፊክ መጨናነቅ እንዳይፈጠር ዝግ የሚደረጉ መንገዶችን የአዲስ አበባ ፖሊስ ጠቅላይ መምሪያ አስታውቋል። 
 
ከቦሌ ዓለም አቀፍ አውሮፕላን ማረፊያ ወደ ብራስ እንዲሁም ከቦሌ መድኃኒያለም በአትላስ ወደ ቅዱስ ኡራኤል ቤተ ክርስቲያን የሚወስደው መንገድ በመሪዎቹ ጉባኤ ምክንያት ከዛሬ የካቲት 4 ቀን 2018 ዓ/ም ጀምሮ ሙሉ ለሙሉ ለተሽከርካሪዎች ዝግ የሚደረግ ይሆናል። 

በተጨማሪም በሌሎች እንግዶች በሚያልፉባቸው ዋና ዋና አደባባዮችና የአጀብ መስመሮች አሽከርካሪዎች ቅድሚያ በመስጠትና የትራፊክ ፖሊስ አባላትን ትዕዛዝ በማክበር የተለመደ ቀና ትብብራቸውን እንዲያደርጉ፤ በተጠቀሱት ቦታዎች ለረጅምም ሆነ ለአጭር ጊዜ ተሽከርካሪዎችን ማቆም የተከለከለ መሆኑንም የአዲስ አበባ ፖሊስ ጠቅላይ መምሪያ እያስታወቀ አጠራጣሪ ነገሮች ሲያጋጥሙም በነጻ የስልክ መስመሮች 990፣ 991፣ 987፣ 816 እንዲሁም በ011-1-26-43-59፣ 011-5-52-63-02/03፣ 011-5-52-40-77፣ 011-5-54-36-78 እና 011-5-54-36-81 እንዲሁም በእጅ ስልኮች የዜጎች ተሳትፎ መተግበሪያን (Citizen Engagement Application) EFPApp በመጠቀም ጥቆማ መስጠት እንደሚገባም ጥሪውን ያስተላልፋል። 
 
 ለተጨማሪ የመረጃ አማራጮች
  https://linktr.ee/addisababacommunication


Comments

ምንም አልተገኘም.

አስተያየቶችዎን ይተዉት.