ዛሬ በመንግስት እና በግል አጋርነት መርሃ ግብር ከጊፍት ሪል እስቴት ጋር የ4 ሺሕ መኖሪያ ቤቶችን ግንባታ አስጀምረናል። ከንቲባ አዳነች አቤቤ
በመጀመሪያ ዙር ግንባታቸውን ያስጀመርናቸው 4 ሺሕ መኖሪያ ቤቶች ከ 14 እስከ 22 ወለል ያላቸው ዘመናዊ ህንጻዎች ሲሆኑ፣ የግንባታ ተገቢ ቅድመ ዝግጅቱን አጠናቅቆ ወደ ስራ የገባውን ጊፍት ሪል እስቴት በነዋሪዎቻችን ስም ላመሰግን እወዳለሁ።
የመኖሪያ ቤት ችግርን ለመቅረፍ የሚያስችሉ አዳዲስ አማራጮችን ከህግና አሰራር ጋር በማጣጣም ተግባራዊ በማድረግ አዲስ አበባን ምቹ የስራና የመኖሪያ ከተማ ለማድረግ መስራታችንን ቀጥለናል።
ፈጣሪ ኢትዮጵያን እና ህዝቦቿን ይባርክ!
ከንቲባ አዳነች አቤቤ
Comments
ምንም አልተገኘም.
አስተያየቶችዎን ይተዉት.