ሁለተኛውን የጣሊያን-አፍሪካ ጉባዔ በጋራ በምናስ...

image description
- ውስጥ Current Affairs    0

ሁለተኛውን የጣሊያን-አፍሪካ ጉባዔ በጋራ በምናስተናግድበት በዚህ ወቅት፣ ጠቅላይ ሚኒስትር ጆርጂያ ሜሎኒን ወደ ኢትዮጵያ እንኳን ደህና መጡ ስል ታላቅ ደስታ ይሰማኛል።

ይህ አጋጣሚ ዲፕሎማሲያዊ ስብሰባ ብቻ ሳይሆን፣ በጣሊያንና በአፍሪካ ሀገራት መካከል ያለውን ጠንካራ አጋርነት ማሳያ ነው።  ይህም አጋርነት በመከባበር፤ በጋራ ኃላፊነትና ለዘላቂ ዕድገት ባለን የጋራ ርዕይ ላይ የተመሠረተ ነው። የጠቅላይ ሚኒስትር ሜሎኒ ጉብኝት በንግድ፣ በኢንቨስትመንት፣ በኢነርጂ፣ በመሠረተ ልማት፣ በግብርና እና በፈጠራ ዘርፎች የቀጠለውን ትብብራችን ለማጠናከር  ያለንን የጋራ ቁርጠኝነት የሚያረጋግጥ ነው።

ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ (ዶ/ር)


Comments

ምንም አልተገኘም.

አስተያየቶችዎን ይተዉት.