ዛሬ ከክብርት ቀዳማዊት እመቤት ዝናሽ ታያቸው እና ከሌሎች የአፍሪካ ሀገራት ቀዳማዊ እመቤቶች ጋር በመሆን፣ በአድዋ ድል መታሰቢያ ሙዚየም ፍሬያማ ቆይታ አድርገናል።
በቆይታችን የቀደምት ጀግኖቻችንን ታላቅ የታሪክ አሻራ በጋራ እያደነቅንና በተለይም የሴት አርበኞቻችንን ተጋድሎ እያወሳን ለእህቶቻችን ገልፀናል። ወደፊትም በአፍሪካዊ እህትማማችነት የአንድነትና የጽናት መንፈስን ይበልጥ ልናጎለብተው በሚገባን ሀሳብ እየተወያየን፣ ደስ የሚል የምሳ ጊዜ አሳልፈናል።
ፈጣሪ አፍሪካን እና ሕዝቦቿን ይባርክ !
ከንቲባ አዳነች አቤቤ
Comments
ምንም አልተገኘም.
አስተያየቶችዎን ይተዉት.