39ኛው የአፍሪካ ሕብረት የመሪዎች ጉባኤ እና 2ኛው የጣሊያን-አፍሪካ ጉባኤ ከወትሮው በተለየ ታላቅ ድምቀትና ስኬት ተጠናቋል።
ጉባኤዎቹ በውቧ መዲናችን አዲስ አበባ ፍጹም ስኬታማ በሆነ መንገድ መካሄዱ፤ እንግዶቻችን የኢትዮጵያዊያንን ለዘመናት የዘለቀ እንግዳ ተቀባይነት እንዲሁም የመዲናችንን አስደናቂ ለውጥና ለጉባኤዉም ትልቅ ሞገስ በመሆኑ ጭምር ነዉ።
መላው የከተማችን ነዋሪዎች ላሳያችሁት እንግዳ አክባሪነት፣ ትዕግስትና አጋርነት ፣ የአገልግሎት ሰጪ ተቋማት ለሰጣችሁት ጥራት ያለው እና ቀልጣፋ አገልግሎት፤ ከተማችንን ሁሌም አዲስ ገፅታ እና መንፈስ በማላበስ ይህ ጉባኤ እንዲሳካ ላደረጋችሁ የከተማችን አመራሮች እና ሰራተኞች፤ በተለይም ከካዛንቺስ እስከ ቦሌ ብራስ ያላችሁ የግል ተቋማትና ግለሰቦች ለሌት ተቀን ትጋታችሁና ቀና ትብብራችሁ፤ እንዲሁም ከነዋሪው ጋር በመቀናጀት በቁርጠኝነት ለሠራችሁ የጸጥታ አካላት በራሴና በከተማ አስተዳደሩ ስም ላቅ ያለ ምስጋናዬን አቀርባለሁ።
ፈጣሪ ኢትዮጵያን እና ሕዝቦቿን ይባርክ!
ከንቲባ አዳነች አቤቤ
Comments
ምንም አልተገኘም.
አስተያየቶችዎን ይተዉት.