ክቡር ጠቅላይ ሚኒስትራችን ዶ/ር ዐቢይ አሕመድ በገበታ ለሸገር እንዲሁም በተለያዩ የከተማችን የልማት ስራዎች ሃሳብ ከማመንጨት ጀምሮ ፕሮጀክቶቹን ወርዶ በመምራት ከተማችንን እንደ ስሟ ውብ እና ፅዱ ለማድረግ በርካታ ስራዎችን በመስራት ላይ ይገኛሉ።
ክቡር ጠቅላይ ሚኒስትር ዶ/ር ዐቢይ ከተማችንን ውብ፣ ፅዱና ለነዋርዎቿ ምቹ የማድረግ ራዕያቸው አካል የሆነ “ጽዱ ጎዳና - ኑሮ በጤና” የሚል አዲስ ሃሳብ የአፍሪካዊያን መዲና በሆነችው አዲስ አበባ ጀምረዋል።
ይህ አዲስ ተግባር ነዋሪዎቻችንን በሚያሳፍር መልኩ በየመንገዱ ከመፀዳዳት ይልቅ፣ የከተማ ውበትን በሚጨምር መልኩ፣ ጤናማ አካባቢንም ለመፍጠር የሚያስችል ሲሆን ለነዋርዎቿ ምቹ ከተማ ለመፍጠር ጠቅላይ ሚኒስትራችን በጀመሩት በዚህ ታላቅ ተግባር ላይ ከማንም በላይ መላው አመራራችን እና ተጠቃሚ የሆኑ የከተማችን ነዋሪዎች በንቃት እንዲሳተፍ ጥሪ ማስተላለፍ እወዳለሁ።
ፈጣሪ ኢትዮጵያን እና ህዝቦቿን ይባርክ
ከንቲባ አዳነች አቤቤ
Comments
ምንም አልተገኘም.
አስተያየቶችዎን ይተዉት.