ከቱርክዬ ሪፐብሊክ ፕሬዝዳንት ረጀብ ጠይፕ ኤርዶጋን ጋር ዘለግ ያለ ውይይት አድርገናል።
ውይይታችን በኢትዮጵያ እና በቱርክዬ መካከል ያለውን ዘላቂ ወዳጅነትና ጠንካራ ትብብር ይበልጥ ያጠናከረ ነው። በስትራቴጂካዊ የትብብር መስኮች ላይ የሃሳብ ልውውጥ ያደረግን ሲሆን፤ የሁለቱን ሀገራት ጥቅም የሚያስከብሩ አጋርነቶችን ለማሳደግ ያለንን የጋራ ቁርጠኝነት ዳግም አረጋግጠናል። ዘላቂው ግንኙነታችን ሁለቱ ሀገሮችን የሚያስተሳስረውን ወዳጅነት ይበልጥ እንደሚያጠናክረው ሙሉ እምነት አለኝ።
ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ (ዶ/ር)
Comments
ምንም አልተገኘም.
አስተያየቶችዎን ይተዉት.