የኬንያ ብሔራዊ ምክር ቤት አባሉ ያደነቋት ውቧ...

image description
- ውስጥ Current Affairs    0

የኬንያ ብሔራዊ ምክር ቤት አባሉ ያደነቋት ውቧ አዲስ አበባ

ሰሞኑን በኬንያ የብሔራዊ ምክር ቤት አባል ጁኔት መሐመድ የተሰጠው ምስክርነት የኢትዮጵያን የለውጥ ጉዞ አዲስ ከፍታ ላይ የሚያሳይ ሆኗል። የምክር ቤት አባሉ የአፍሪካ የዲፕሎማሲ መናኸሪያ የሆነችውን አዲስ አበባን "የአፍሪካዋ አዲሷ ዱባይ" ሲሉ አወድሰዋታል።

ባለፉት ጥቂት ዓመታት በከተማዋ የታየው ግዙፍ የመሠረተ ልማት ግንባታ፣ የፓርኮች ልማትና የከተማ ውበት ሥራዎች አዲስ አበባን ለነዋሪዎቿ ብቻ ሳይሆን ለጎብኚዎችም ማራኪና ዘመናዊ መዳረሻ አድርጓታል ብለዋል።

የፓርላማ አባሉ አዲስ አበባን ከአደጉት ሀገራት ምርጥ ከተሞች ጋር ያነጻጸሯት በሕንፃዎቿ ዘመናዊነት ብቻ ሳይሆን፣ በከተማዋ ያለው አስተማማኝ ሰላም ጭምር መሆኑን ጠቁመዋል።

"ማንም ሰው በሌሊት በነፃነትና ያለ ሥጋት መንቀሳቀስ የሚችልባት ከተማ ናት።" በማለት አዲስ አበባን የገለጿት ሲሆን፣ ይህ የሰላምና የልማት ቅንጅት ለሌሎች የአፍሪካ ከተሞች ትልቅ ትምህርት የሚሰጥ መሆኑን አመልክተዋል።

ጁኔት መሐመድ አክለውም፣ ኬንያም ሆነች ሌሎች የአፍሪካ ሀገራት የልማት ተሞክሮን ለመቅሰም ወደ ሩቅ ሀገራት ከመመልከት ይልቅ፣ እዚሁ አጠገባቸው ያለችውን ጎረቤታቸውን ኢትዮጵያን አርዓያ ማድረግ አለባቸው ብለዋል።

የኬንያ ምክር ቤት አባላት ለጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አህመድ (ዶ/ር) እና ለኢትዮጵያ ሕዝብ ያላቸውን አክብሮት ገልጸዋል። ኢትዮጵያ በታሪኳ ቅኝ ተገዝታ የማታውቅ የጥቁር ሕዝቦች የነፃነት ተምሳሌት መሆኗን በማስታወስ፣ አሁን ደግሞ በኢኮኖሚው ዘርፍ እያስመዘገበችው ያለው ድል ለጥቁር ሕዝቦች ሁሉ ኩራት መሆኑን አረጋግጠዋል።

ይህ የኢትዮጵያ ስኬት አዲስ አበባን የአፍሪካ የንግድና የቱሪዝም ማዕከል እንድትሆን ከማገዙም በላይ፣ አህጉሪቱ በራሷ አቅም መበልፀግ እንደምትችል በተግባር ያሳየ ሆኗል። 
 
 ለተጨማሪ የመረጃ አማራጮች
  https://linktr.ee/addisababacommunication


Comments

ምንም አልተገኘም.

አስተያየቶችዎን ይተዉት.