የቱሉ ካፒ የወርቅ ልማት ፕሮጀክት የተፈጥሮ ኃብታችንን እንዴት ለሀገር እና ሕዝብ ጥቅም በኃላፊነት ልንጠቀምበት እንደምንችል የሚያሳይ አይነተኛ ምሳሌ ነው።
በምዕራብ ወለጋ ገንጂ ዞን የሚገኘው ፕሮጀክቱ በመንግሥት እና የግል ኢንቨስተሮች ትብብር እየተሠራ የሚገኝ ነው። ከኢኮኖሚያዊ ጠቀሜታው ባሻገር ፕሮጀክቱ ለትምህርት፣ የመንገድ ልማት፣ የጤና ተቋማት እና ዘመናዊ የመኖሪያ ቤት ግንባታን የማነቃቃት አቅም አለው። በጉብኝታችን ወቅት እንደተመለከትኩት የፕሮጀክቱ ፋይዳ በአንድ የተወሰነ ብቻ ሳይሆን የአካባቢውን ማኅበረሰብ የበለጠ ለልማት በማነሳሳት ከፍ ያለ ሚናውን እንደሚያስቀጥል እምነቴ የፀና ነው።
ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ (ዶ/ር)
ለተጨማሪ የመረጃ አማራጮች
https://linktr.ee/addisababacommunication
Comments
ምንም አልተገኘም.
አስተያየቶችዎን ይተዉት.