የአርጆ ዲዴሳ የመስኖ ልማት ፕሮጀክትን የጎበኘሁ ሲሆን የደረሰበት ደረጃም አስደናቂ መሆኑን ተመልክቻለሁ።
ይኽ ትልቅ ፕሮጀክት በቅርብ ዓመታት ግንባታው ተፋጥኖ ወደ መጠናቀቂያው ተቃርቧል። ለአገልግሎት በሚበቃበት ጊዜም የተለያዩ የአዝርዕት ልማትን በመደገፍ እንደሀገር የጀመርነውን የምግብ ሉዓላዊነት ጥረቶች እና በሺዎች የሚቆጠሩ አርሶአደሮችን በመጥቀም ግብርናውን የሚያሻግር ይሆናል። ይኽ ፕሮጀክት ባላሰለሰ ጥረት እና የታቀደለትን ግብ በማሳካት የአካባቢውን ማኅበረሰብ ኑሮ ከፍ እንደሚያደርግ እተማመናለሁ።
ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ (ዶ/ር)
Comments
ምንም አልተገኘም.
አስተያየቶችዎን ይተዉት.