አርሶአደሮቻችን እያመረቱ ብቻ አይደለም፤ ከመዋጮ...

image description
- ውስጥ Current Affairs    0

አርሶአደሮቻችን እያመረቱ ብቻ አይደለም፤ ከመዋጮዎቻቸውም እሴት እያፈሩ ይገኛሉ።ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ (ዶ/ር)

በ1996 ዓ.ም የተመሠረተው የጊቤ ዲዴሳ የገበሬዎች የኅብረት ሥራ ማኅበር 207 የመጀመሪያ ደረጃ ማኅበራትን ያቀፈ ነው። አንድ መቶ ስልሳ ሰባት ሺህ ገበሬዎችን የሚያገለግለው ማኅበሩ፤ አሁን ላይ የግብርና ግብዓቶችን ከማቅረብ ተሻግሮ የምርት እሴትን ወደመጨመር አሳድጓል። ማኅበሩ በቅርቡ ዘመናዊ የእህል ወፍጮ ያቋቋመ ሲሆን በቀን 1200 ኩንታል የበቆሎ ዱቄት የማምረት አቅም አለው። በ2.8 ሄክታር መሬት ላይ የተገነባው ፋብሪካ ለአካባቢው ጊዜያዊ እና ቋሚ የሥራ እድሎችን ፈጥሯል።

ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ (ዶ/ር)


Comments

ምንም አልተገኘም.

አስተያየቶችዎን ይተዉት.