የዓለም መሪዎችን ያስደመሙ፣ የቱሪስቶችን ቀልብ የገዙ እና ለነዋሪዎቿ ምቹ የዓይን ማረፍያ የሆኑ የልማት ስኬቶቿ በውድ የሀገሯ ልጆች አቅም፣ሞያ እና ሁለንተናዊ እሳቤዎቿ ነው።
ውቧ አዲስ አበባ፤-
በኢትዮጵያውያን እጆች የጥበብ አሻራ ያረፈባቸው ዘመኑን የዋጁ ፣በፈጣን የከተማ ልማት ማሻሻያ እና በዘመናዊ የትራፊክ ፍሰት ላይ እየተከናወኑ ያሉ የመሰረተ ልማት ዝርጋታዎች ከተማዋን እንደ-አዲስ በፈጣን እድገትና ዘመናዊ ገፅታ የዓለምን ትኩረት እንድትስብ አድርጓታል፡፡
እነዚህ በሁለንተናዊ መልኩ በመዲናዋ እየተከናወኑ ያሉና የዓለምን ትኩረት እየሳቡ የሚገኙ የኮሪደር የልማት ስራዎች፣ በኢትዮጵያውያን የተገነቡ መሆናቸውና ከተማዋ ከመቸዉም ጊዜ በላይ ፕሮጀክት ጀምሮ የመጨረስ እና በውስጥ አቅም የመለወጥ ብቃት ለአፍሪካውያን ምሳሌ እየሆነች መሆኑ ወደ አዳዲስ ምእራፍ መሸጋገሪያ የዚህ ዘመን አሻራ ነዉ፡፡
እዉነታዉ ይህ ሆኖ ሳለ በመሰረታዊ ሁለንተናዊ ብልፅግናችን እና ፍፁም በሆነ የከተማ ዕድገታችን ጀርባ “ሌሎች” እንዳሉ ተደርጎ የሚሰራጩ የተለመዱ “በሬ ወለደ” መሰረተ-ቢስ መረጃዎች የመቻላችን እውነት ካለመረዳት እንደሆነ እናምናለን።
Comments
ምንም አልተገኘም.
አስተያየቶችዎን ይተዉት.