ዛሬ በከተማችን ለ5ኛ ጊዜ የሚካሄደውን የኢትዮጵ...

image description
- ውስጥ Current Affairs    0

ዛሬ በከተማችን ለ5ኛ ጊዜ የሚካሄደውን የኢትዮጵያ ታምርት ንቅናቄ “ኢትዮጵያ ታምርት፣ አዲስ አበባ ትበልፅግ” በሚል መሪ ቃል በይፋ አስጀምረናል።

ንቅናቄው ባለፉት የለውጥ ዓመታት በተለያዩ ማነቆዎች ተዘግተው የነበሩ አምራች ኢንዱስትሪዎችን ዳግም ወደ ምርታማነት በመመለስ፤ የፋይናንስና የማምረቻ ቦታዎችን በማመቻቸት፤ የገበያ ትስስር በመፍጠር እንዲሁም የእውቀትና የቴክኖሎጂ ሽግግር እንዲኖር በማድረግ ረገድ አስተዳደራችን የወሰዳቸው እርምጃዎች ፍሬ እያፈሩ መሆናቸውን የተመለከትንበት ነው። 

በዚህም በዘርፉ በከተማችን እየተከናወኑ ባሉ ተግባራት ተጨባጭ ለውጥ ማስመዝገብ ችለናል።

በተለይም በተኪ ምርቶች እድገት ረገድ የአገር ውስጥ ምርት ተጠቃሚነት ባህል እያደገ መጥቷል። አምራቾች በቀጣይም በየዕለቱ በምርት ጥራት ላይ በመላቅ ተወዳዳሪነታችሁን እያሳደጋችሁ እንድትሄዱ አደራ ለማለት እወዳለሁ።

የተለያዩ የጨርቃጨርቅ (ቴክስታይል)፣ የሕክምና፣ የቆዳና የቆዳ ውጤቶች እንዲሁም የኤሌክትሮኒክስ ምርቶች በስፋት የቀረቡበት ይህ ንቅናቄ፤ ለሚቀጥለው አንድ ሳምንት እጅግ ውብና ከሁሉም የከተማው ክፍል ለትራንስፖርት አመቺ ሆኖ በተገነባው በአዲስ አበባ ኮንቬንሽን ሴንተር የሚቆይ ይሆናል። መላው የከተማችን ነዋሪዎች የከተማችን አምራች ኢንዱስትሪዎች ያመረቷቸውን ውጤቶች እንድትጎበኙና እንድትሸምቱ ጥሪዬን አቀርባለሁ።

ፈጣሪ ኢትዮጵያንና ሕዝቦቿን ይባርክ!
ከንቲባ አዳነች አቤቤ


Comments

ምንም አልተገኘም.

አስተያየቶችዎን ይተዉት.