የአስተዳደራችንን የዘጠኝ ወራት ዕቅድ አፈጻጸም ግምገማ አጠናቅቀናል::ከንቲባ አዳነች አቤቤ
ባለፉት ዘጠኝ ወራት ከፈተናዎቻችን ባሻገር አዲስ አበባን እንደስሟ ውብ ለነዋሪዎችዋ ምቹ እንዲሁም የቱሪስት መዳረሻ ዓለም አቀፍ የስበት ማዕከል ለማድረግ የሰነቅነውን ራዕይ ዕውን ማድረግ ያስቻሉ ፈጠራ የታከለባቸው አዳዲስ አሰራሮችን በመከተል ፣ ጠንካራ የስራ ባህል በመገንባት እና የአመራር ቁርጠኝነትን እና ቅንጅትን በማረጋገጥ የጀመርናቸው ፕሮጀክቶችን በፍጥነት ጀምረን በመጨረስ ለህዝባችን አገልግሎት ክፍት እንዲሆኑ አድርገናል::
የነዋሪውን የኑሮ ጫና አቅልለው ተስፋ ያለመለሙ የሰው ተኮር ስራዎቻችንም የበርካቶችን ሸክም ያቀለሉ የአቅመ ደካሞችንና የሀገር ባለውለታዎችን እምባ አብሰው ማህበራዊ ፍትህን ያነገሱ የመሬት ዲጂታላይዜሽን እና የገቢ አሰባሰብ ስራችን ውጤት ካገኘንባቸው ስራዎች ውስጥ የሚጠቀሱ ናቸው::
ከተማችንን ውብ፣ ጽዱ እና ለመኖር ምቹ ለማድረግ የጀመርነው የኮሪደር ልማት ስራችን ለነዋሪዎቻችን መልካም እድል የፈጠረ ሲሆን ግምገማችን በቀሪ ወራት ጥንካሬዎቻችንን በማጽናት ድክመቶቻችን ከነመንስዔዎቻቸው ተነቅሰው እንዲወጡ እና ለላቀ ውጤታማ ስራ የሚያተጉ እንዲሁም የነዋሪዎች ቅሬታ ምንጭ የሆኑትን ቀልጣፋና ከተማዋን የሚመጥን የአገልግሎት አሰጣጥ ፣ ሌብነት እና ጉቦኝነት ላይ መሰረታዊ ለውጥ ለማምጣት የምንሰራ ይሆናል::
እየፈጠርን ፈጥነን በመተግበር ቃል በገባነው ልክ አዲስ አበባን እንደስሟ ውብ ለማድረግ በትጋት ማገልገላችንን እንቀጥላለን::
ፈጣሪ ኢትዮጵያን እና ህዝቦቿን ይባርክ!
ከንቲባ አዳነች አቤቤ
Comments
ምንም አልተገኘም.
አስተያየቶችዎን ይተዉት.