በግብርናው ዘርፍ ለውጥ ለማምጣት እየተከናወኑ ካሉ ስራዎች መካከል፤ ያሉንን የገጸ ምድርና የከርሰ ምድር ውሃ ሃብቶች ለመስኖ ልማት የማዋሉ ስራ ዋነኛው ነው።
ከዚህ ቀደም ጥቅም ሳይሰጡ የቆዩ በርካታ ቦታዎች አሁን ላይ በመስኖ ወደ ግብርና ልማት ማዕከልነት እየተቀየሩ ነው። የብላቴ ወንዝ የሚገኝበት አካባቢ ደግሞ ለዚህ ተጠቃሽ አብነት ነው። በአካባቢው የግል ባለሃብቶችን በማሳተፍ ሰፋፊ የፍራፍሬ ልማቶች እየተከናወኑ ይገኛል። ይህም የምግብ ሉዓላዊነትን ለማረጋገጥ የሚደረገውን ጥረት በእጅጉ የሚያግዝ ነው።
ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አህመድ(ዶ/ር)
Comments
ምንም አልተገኘም.
አስተያየቶችዎን ይተዉት.