በአዘርባጃን ባደረግኩት የመጀመሪያ ይፋዊ የሥራ ጉብኝት ፕሬዝዳንት ኢልሃም አሊዬቭ ላደረጉልኝ ሞቅ ያለ እና የተከበረ አቀባበል ልባዊ ምስጋናዬን አቀርባለሁ። የጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ (ዶ/ር) መልዕክት
ባለፉት ጥቂት ዓመታት በአቪዬሽን ዘርፍ፣ በኢንዱስትሪ ፓርኮች እና በነፃ የንግድ ቀጣናዎች፣ እንዲሁም በኢትዮጵያ ኢንቨስትመንት ሆልዲንግስ እና በአዘርባጃን አቻው መካከል በተደረጉ የኢኮኖሚ ትብብሮች ላይ በመመስረት አጋርነታችን በየጊዜው እያደገ መጥቷል።
እነዚህ የትብብር ዘርፎች ለሁለትዮሽ ግንኙነታችን መጠናከር መሠረት የጣሉ ሲሆን፣ ዛሬ ባደረግነው ጥልቅ ውይይትም ግንኙነታችንን እና ትብብራችንን ይበልጥ ለማጠናከር እና ወደ ላቀ ደረጃ ለማሳደግ ተስማምተናል።
በዛሬው ዕለትም በመከላከያ እና በሌሎች ዘርፎች ዙሪያ የመግባቢያ ሰነዶች ፊርማ ሥነ-ሥርዓት ላይ ተገኝተናል።
Comments
ምንም አልተገኘም.
አስተያየቶችዎን ይተዉት.