የዓድዋ ድል ለነፃነታችን መሰረት እንደሆነ ሁሉ፥ የኮሪደር ልማት ስራዎቻችንም የከተማዋን የኢኮኖሚ ዕድገት መሰረት ጥለዋል!
የዓድዋ ድል የጥቁር ህዝቦች የነፃነት ተምሳሌት ብቻ ሳይሆን የአንድነት፣ የጥረትና እቅድ ውጤት ነው። አዲስ አበባ የዚህን ታላቅ ታሪካዊ ድል መንፈስ በመውሰድ በልማትና በመልካም አስተዳደር አዲስ ምዕራፍ እየከፈተች ትገኛለች።
ከዛሬ 130 ዓመታት በፊት አባቶቻችንና እናቶቻችን በዓድዋ ተራሮች ላይ በቁርጠኝነት ተባብረው አዲስ ታሪክ እንደሰሩ ሁሉ የከተማ አስተዳደሩ ተመሳሳይ ቁርጠኝነት ይዞ እየሰራ ይገኛል።
የዓድዋ ድል ለነፃነታችን መሰረት እንደሆነ ሁሉ የኮሪደር ልማት ስራዎችም የከተማዋን ምቾት፣ ውበት እና የኢኮኖሚ እድገት መሰረት ጥለዋል። እንደ ዓድዋ ጦርነት ስልታዊ አቀራረብ ሁሉ፣ የኮሪደር ልማቱ የከተማዋን የትራፊክ ፍሰት ለማዘመን፣ የእግረኛ መንገዶችን ለማስዋብ እና ለአካባቢ ጥበቃ ተስማሚ የሆኑ አረንጓዴ ቦታዎችን ለመፍጠር እቅድ ይዞ በመንቀሳቀስ ላይ ነው።
ከዚህ በተጨማሪም የመሰረተ ልማት ዝርጋታ፡ የመንገድ፣ የውሃ፣ የመብራት፣ እና የፍሳሽ ማስወገጃ መስመሮችን በማዘመን፣ የአድዋን ድል ዘላቂነት ለማረጋገጥ የተደረገውን አይነት ጥረት፣ ለከተማዋ ዘላቂ የመሰረተ ልማት መሰረት አስቀምጧል።
በከተማ አስተዳደሩ እየተሰሩ ያሉ የመልካም አስተዳደር ስራዎች፣ የህዝቡን ጥያቄዎች በቅድሚያ በመመልከት፣ ግልጽነትና ተጠያቂነት ባለው መልኩ አገልግሎት ለመስጠት ያለመ ነው። አዲስ አበባ ለነዋሪዎቿ የምትመች፣ ፍትሃዊ የሀብት ክፍፍል የምታረጋግጥ እና የመንግስት አገልግሎቶችን በቅልጥፍና የምትሰጥ ከተማ እንድትሆን ልዩ ትኩረት በመስጠት እየተሰራ ይገኛል፡፡
የዓድዋ ድል ኢትዮጵያውያን ወደ ብልጽግና የሚዘልቁበት መስፈንጠሪያ ነው። ድሉ በስንቅና በታክቲክ እንደተገኘ ሁሉ የአዲስ አበባ ልማትም በታቀደ በጀትና በቁርጠኛ አመራርና በህዝብ ንቁ ተሳትፎ እውን እየሆነ ነው።
Comments
ምንም አልተገኘም.
አስተያየቶችዎን ይተዉት.