130ኛው የአድዋ ድል መታሰቢያ በዓል የካቲት 2...

image description
- ውስጥ Current Affairs    0

130ኛው የአድዋ ድል መታሰቢያ በዓል የካቲት 23 ቀን 2018 ዓ/ም ፒያሳ አካባቢ በሚገኘው የዓድዋ ድል መታሰቢያ ሙዚየም የሚከበር ሲሆን ለበዓሉ መከበር አስፈላጊውን ቅድመ ዝግጅት አጠናቆ ወደ ስራ መግባቱን የፀጥታና ደህንነት የጋራ ግብረ ኃይል አስታወቀ፡፡

በዓሉ በሚከበር ዕለት የትራፊክ መጨናነቅ እንዳያጋጥም እና አሽከርካሪዎች አማራጭ መንገዶችን እንዲጠቀሙ የተወሰኑ መንገዶች ለተሽከርካሪዎች ዝግ እንደሚሆኑም የአዲስ አበባ ፖሊስ ጠቅላይ መምሪያ አስታውቋል። በዚህ መሰረት:-
👉 ከቸርችል ጎዳና በቴዎድሮስ አደባባይ ምኒልክ አደባባይ የሚወስደው መንገድ ባንኮ ዲሮማ መብራት፣
👉 ከአራት ኪሎ በራስ መኮንን ወደ ዳግማዊ ምኒሊክ አደባባይ የሚወስደው መንገድ ራስ መኮንን ድልድይ፣ 
👉 ከመነን አካባቢ እና የካቲት 12 ሆስፒታል በአፍንጮ በር ወደ ዳግማዊ ምኒልክ አደባባይ የሚወስደው መንገድ አፍንጮ በር፣ 
👉 ከእሪ በከንቱ በኤሌክትሪክ ህንፃ ወደ ዳግማዊ ምኒልክ አደባባይ የሚወስደው መንገድ ቀይ ባህር ኮንዶሚኒየም፣
👉 ከአዲሱ ገበያ በሰሜን ሆቴል ወደ ዳግማዊ ምኒልክ አደባባይ የሚወስደው መንገድ ሰሜን መብራት፣ 
👉 ከመርካቶ በአቡነ ጴጥሮስ ወደ ዳግማዊ ምኒለሰክ አደባባይ የሚወስደው መንገድ ደጃዝማች ኃብተ ጊዮርጊስ ድልድይ፣ 
👉 ከእንቁላል ፋብሪካ በቅዱስ ዮሐንስ ቤተክርስቲያን ወደ ዳግማዊ ምኒልክ አደባባይ የሚወስደው መንገድ ቅዱስ ዮሐንስ መብራት ላይ ነገ የካቲት 23 ቀን 2018 ዓ/ም ከንጋቱ 12:00 ጀምሮ ለተሽከርካሪዎች ዝግ የሚደረግ ሲሆን
በተጠቀሱት ቦታዎች ለአጭርም ሆነ ለረዥም ሰዓት ተሽከርካሪ አቁሞ መሄድ ፈፅሞ የተከለከለ መሆኑን አሽከርካሪዎች አውቀው ሌሎች አማራጭ መንገዶችን እንዲጠቀሙ የአዲስ አበባ ፖሊስ ጠቅላይ መምሪያ እያሳሰበ ለፀጥታ ስጋት የሆኑ አጠራጣሪ ነገሮች ሲያጋጥሙም በነጻ የስልክ መስመሮች 990፣ 991፣ 987፣ 816 እንዲሁም በ011-1-26-43-59፣ 011-5-52-63-02/03፣ 011-5-52-40-77፣ 011-5-54-36-78 እና 011-5-54-36-81 እንዲሁም በእጅ ስልኮች የዜጎች ተሳትፎ መተግበሪያን (Citizen Engagement Application) EFPApp በመጠቀም ጥቆማ መስጠት እንደሚገባም ጥሪውን ያስተላልፋል።


Comments

ምንም አልተገኘም.

አስተያየቶችዎን ይተዉት.