በኮሪደር ልማት ምክንያት የተነሳውን የኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋሕዶ ቤተክርስቲያን ሕንጻ የመልሶ ግንባታ ስራን ብፁዕ ወቅዱስ አቡነ ማትያስ የኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋሕዶ ቤተክርስቲያን ፓትርያርክ እና ሌሎች የሀይማኖቱ አባቶች በተገኙበት ዛሬ አስጀምረናል።ከንቲባ አዳነች አቤቤ
የኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋህዶ ቤተክርስቲያን የከተማ ኘላን እና ልማት እንዲጠበቅ፣ ከተማችን እንድትለማ፣ እንድትዘምን እና የተሻለ ዲዛይን እንዲተገበር በርካታ ትብብር በማድረግ ላይ የምትገኝ ሲሆን ይህ ዛሬ መልሶ ግንባታ ስራውን ያስጀመርነው ህንጻ የዚህ አንዱ ማሳያ ነው።
ይህ ህንጻ ባለ 4 ወለል የነበረ ሲሆን አዲሱ ግንባታ ለፓርኪንግ ግልጋሎት የሚውል አንድ ቤዝመንት የሚጨምር ዘመናዊ ባለ አራት ወለል ህንጻ ሆኖ ከአካባቢው ልማት፣ ፕላን፣ በዙሪያው ካሉ ሌሎች ቅርሶች እንዲሁም ከዓድዋ ድል መታሰቢያ ጋር የሚናበብ ነው። ግንባታውን በአጭር ጊዜ ውስጥ አጠናቅቀን ለቤተክርሰቲያኗ የምናስረክብ ይሆናል።
የኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋህዶ ቤተክርስቲያን አባቶች የልማት ኮሪደር ስራውን በመደገፍ ከጎናችን ስለቆሙ ከልብ ላመሰግናቸው እወዳለሁ።
ፈጣሪ ኢትዮጵያን እና ህዝቦቿን ይባርክ
ከንቲባ አዳነች አቤቤ
Comments
ምንም አልተገኘም.
አስተያየቶችዎን ይተዉት.