የባሕር በር ማጣታችን የታሪካዊ ውድቀት ውጤት ነ...

image description
- ውስጥ Current Affairs    0

የባሕር በር ማጣታችን የታሪካዊ ውድቀት ውጤት ነው- ፊልድ ማርሻል ብርሃኑ ጁላ

የጦር ኃይሎች ጠቅላይ ኢታማዦር ሹም ፊልድ ማርሻል ብርሃኑ ጁላ 130ኛውን የዓድዋ ድል በዓል ምክንያት በማድረግ ባስተላለፉት ጠንካራ መልዕክት የባሕር በር ማጣታችን የታሪካዊ ውድቀት ውጤት መሆኑን ገልጸዋል።  

ፊልድ ማርሻሉ ትላንት ግድቡን እንዳንገነባ ሲያደናቅፉ የነበሩ ኃይሎች ዛሬ ህጋዊ የባሕር በር ጥያቄያችንን እየተቃወሙ ነው ያሉ ሲሆን፣ ሠራዊቱ የሀገር አጥር በመሆን በወረሰው የዓድዋ ጀግኖች መንፈስ ማንኛውንም የጠላቶችና የከሃዲዎችን ሴራ ለመመከት ዝግጁ መሆኑንም አረጋግጠዋል። 

ፊልድ ማርሻል ብርሃኑ ጁላ አክለውም ሕዝቡ እንደ ዓድዋ አርበኞች ሁሉ ከሠራዊቱ ጎን በመቆም ብሔራዊ ጥቅምን እንዲያስከብር ጥሪ ያቀረቡ ሲሆን፣ የኢትዮጵያ ብሔራዊ ጥቅሟን ለመጠበቅ የታሪካዊ ጠላቶችንና የዘመኑ ባንዳዎችን ሴራ እንደምትቀለብስ ገለጹ።

ጠቅላይ ኢታማዦር ሹሙ ዓድዋ የጥቁር ሕዝቦች የነፃነት ምልክት ከመሆኑ ባለፈ፣ አርበኛን ከባንዳ የለየ የታሪክ ክስተት እንደሆነም  በዚሁ ወቅት ገልጸዋል።

የባሕር በር ማጣት የታሪካዊ ስህተት ውጤት መሆኑን ጠቅሰው፤ ይህንን ስህተት ለመድገም የሚሹ ኃይሎችን ሠራዊቱ በማንኛውም መስዋዕትነት እንደሚመክት አረጋግጠዋል።


Comments

ምንም አልተገኘም.

አስተያየቶችዎን ይተዉት.