በዛሬው ዕለት ሚያዚያ 21 ቀን 2016 ዓ.ም ን...

image description
- ውስጥ Current Affairs    0

በዛሬው ዕለት ሚያዚያ 21 ቀን 2016 ዓ.ም ንጋት ላይ በቦሌ ክ/ከተማ በወረዳ 11 ወረገኑ እየተባለ በሚጠራው አካባቢ የጣለዉን ዝናብ ተከትሎ በተከሰተ የጎርፍ አደጋ የአራት ሰዎች ህይወት አልፏል።

የከተማ አስተዳደሩ ማስተር ፕላናቸዉን ያልተከተሉ የወንዝ ዳርቻ ግንባታዎች ህብረተሰቡን ለጎርፍ አደጋ እንደሚያጋልጡ በጥናት በመለየት ይህንን የአደጋ ስጋትና ተጋላጭነት በመሠረታዊነት የሚፈታ ፕላኑን የጠበቀ ዘላቂ የመፍትሄ ስራዎችን እያከናወነ እንደሚገኝ ይታወቃል።

የከተማ አስተዳደሩ በደረሰው በዚህ ድንገተኛ አደጋ ምክንያት ህይወታቸውን ላጡ ወገኖቻችን የተሰማውን ጥልቅ ሀዘን ይገልጻል::

በመሆኑም ተመሳሳይ አደጋዎች እንዳያጋጥሙ ህብረተሰቡ ከከተማ አስተዳደሩና ከእሳትና አደጋ ስጋት ስራ አመራር ኮሚሽን የሚተላለፉ የጥንቃቄ መልእክቶችን ተግባራዊ እንዲያደርግ ያሳስባል::

ለእሳትና ለሌሎች ድንገተኛ አደጋዎች እንዲሁም ለአንቡላንስ አገልግሎት በ939 ፈጥነዉ ያሳዉቁ!


Comments

ምንም አልተገኘም.

አስተያየቶችዎን ይተዉት.