ዛሬ ባለፉት 10 ዓመታት በከፍተኛ የአንጎል ውስጥ ውሃ እና የአንጎል ግፊት መጨመር (ሀይድሮሴፋለስ) ምክንያት የአልጋ ቁራኛ የሆነችውን ህፃን ብሌን አሸናፊን በመኖሪያ ቤቷ ተገኝተን ጠይቀናታል።
ህፃን ብሌን ወደ ውጭ ሀገር ሄዳ አስፈላጊውን ህክምና እንድታገኝ በሀኪሞች ቢታዘዝላትም፣ በፋይናንስ እጥረት ምክንያት እስካሁን ሳይሳካላት ቆይቷል።
ለከተማችን ነዋሪዎች ችግር መቃለል ሁሌም እንደምናደርገው ሁሉ፣ ዛሬም ለህክምናዋ የሚያስፈልገውን 4 ሚሊዮን ብር ለወላጅ አባቷ አስረክበናል።
የብሌን አባት ወጣት አሸናፊ በከተማችን በጽዳት ሰራተኝነት ተቀጥሮ እየሰራ፤ ያለ እናት እርዳታ ብሌንን፣ ታናሽ እህቷን፣ ሌላኛዋን አካል ጉዳተኛ እህቱን እና በመከላከያ ሰራዊት ውስጥ አገልግለው ጡረታ የወጡ አቅመ ደካማ እናቱን የሚንከባከብ፣ ለብዙዎች አርአያ የሚሆን ጠንካራ ወጣት ሆኖ አግኝተነዋል።
"በእንቅርት ላይ ጆሮ ደግፍ" እንዲሉ፣ ህፃን ብሌን የታዘዘላትን የፊዚዮቴራፒ ህክምና እንድትከታተል በአሁኑ ወቅት የሚኖሩበት ቤት ለመቆም እንኳን የማይመችና ከህመሟ ባህሪ አንጻር እጅግ አስቸጋሪ ሆኖ አግኝተነዋል። በመሆኑም ቤተሰቡ የተሻለ መኖሪያ ቤት እንዲያገኝ ወስነናል።
ባደረግንላቸው ጥሪ መሰረት ይህንን በጎ ተግባር በመደገፍ፣ የብሌንን አጠቃላይ የህክምና ወጪ ለሸፈኑት ለክቡር ሼህ ሙሀመድ ሁሴን አሊ አል አሙዲ ከልብ የመነጨ ምስጋናዬን አቀርባለሁ።
ፈጣሪ አምላክ ሁሉን ቻይ ነው! የህፃን ብሌን አሸናፊ ፈገግታ ተመልሶ፣ ቆማ የምትሄድበት፣ እንደ እኩዮቿ የምትቦርቅበትና ትምህርት ቤት የምትሄድበት ጊዜ ቅርብ እንዲሆን እንመኛለን።
በተለይም የ7 ዓመት እህቷ የማርያም አሸናፊ፣ ብሌንን ለማጫወት የምታደርገው ጥረት እጅግ ልብ የሚነካ ነው። ፈጣሪ ልፋታችሁን ቆጥሮ እንዲክሳችሁ እመኛለሁ።
ፈጣሪ ኢትዮጵያን እና ሕዝቦቿን ይባርክ!
ከንቲባ አዳነች አቤቤ
Comments
ምንም አልተገኘም.
አስተያየቶችዎን ይተዉት.