ዛሬ በዝቅተኛ የኑሮ ደረጃ ላይ ከሚገኙ ሙስሊም እህትና ወንድሞቻችን ጋር የአብሮነት መገለጫ በሆነችው በውቧ አራዳ ፓርክ የኢፍጣር መርሐ-ግብር አካሂደናል።
በአሁኑ ወቅት ሙስሊሙ ማህበረሰብ በታላቁ የረመዳን ጾም ፣የክርስትና እምነት ተከታዮች በታላቁ ዓቢይ ጾም ወደ ፈጣሪ ይበልጥ የሚቀርቡበት ወቅት ሲሆን ይህም ከወትሮው በተለየ ያለ ሃይማኖት ልዩነት እርስ በእርስ የምንጠያየቅበት፣ የምንደጋገፍበት፣ የምንተሳሰብበትና ‘ምን ጎደለ?’ የምንባባልበት ልዩ ጊዜበመሆኑ በዝቅተኛ የኑሮ ደረጃ ላይ ከሚገኙ ወገኖቻችን ጋር የሚደረገዉ የኢፍጣር ፕሮግራም በሁሉም የከተማችን ክፍለ ከተሞች በስፋት እየተከናወነ ነዉ።
ከተማችንን የመተሳሰብ፣ የመረዳዳትና የመደጋገፍ ተምሳሌት የማድረጋችን ተግባር ይበልጥ ተጠናክሮ ይቀጥላል።
ፈጣሪ ኢትዮጵያን እና ሕዝቦቿን ይባርክ!
ከንቲባ አዳነች አቤቤ
Comments
ምንም አልተገኘም.
አስተያየቶችዎን ይተዉት.