የሴቶች ድምፅ ለእኩልነትና ለበለፀገች ኢትዮጵያ !
ዛሬ ማለዳ፣ በዓለም አቀፍ ደረጃ ለ115ኛ እንዲሁም በኢትዮጵያ ለ50ኛ ጊዜ የሚከበረውን ዓለም አቀፍ የሴቶች ቀንን ምክንያት በማድረግ፤ ከ120 ሺህ በላይ የከተማችን ሴቶች የተሳተፉበት የ5 ኪሎ ሜትር የጎዳና ላይ ሩጫ እና የማስ ስፖርት አካሂደናል።
ለከተማችን አዲስ ውበት በሆነውና ከቦሌ ተርሚናል - አትላስ - ኡራኤል በተገነባው የኮሪደር መስመር ተጀምሮ እስከ ሴቶች አደባባይ በዘለቀው በዚህ የሩጫ ውድድር ላይ፤ ታዋቂ አትሌቶችና የውጭ ሀገር ዜጎችን ጨምሮ በርካታ የመዲናችን ሴቶች በደመቀ ሁኔታ ተሳትፈዋል።
አሁን ላይ ሴቶች በኢትዮጵያ ሁለንተናዊ የብልፅግና እና የእኩልነት ጉዞ ላይ በንቃት በመሳተፍ፣ ተጠቃሚነታቸውን እያረጋገጡና የበኩላቸውን አስተዋፅኦ እያበረከቱ ይገኛሉ። ይህ ሁለንተናዊ ተሳትፎና እኩል ተጠቃሚነት በቀጣይም ተጠናክሮ የሚቀጥል ይሆናል።
እንኳን ለዓለም አቀፉ የሴቶች ቀን አደረሳችሁ!
ፈጣሪ ኢትዮጵያን እና ሕዝቦቿን ይባርክ!
ከንቲባ አዳነች አቤቤ
Comments
ምንም አልተገኘም.
አስተያየቶችዎን ይተዉት.