ማምሻዉን በቴዎድሮስ አደባባይ አካባቢ እጅግ ዘመናዊ ሆኖ የተገነባውን የድል ፕላዛ እና የቁርጡሜ የወንዝ ዳርቻ ልማትን አጠናቀን ለአገልግሎት ክፍት አድርገናል።
በአንድ ወቅት የወንጀለኞች መሸሸጊያና የቆሻሻ መጣያ የነበረውን ስፍራ፤ ዛሬ ውብ፣ ለአይን ማራኪ እና የከተማችን አንዱ የቱሪስት መስህብ አድርገን ገንብተነዋል።
የድል ፕላዛ እና ቁርጡሚ የወንዝ ዳርቻ ልማት ፦
- 21,906 ካሬ ሜትር የወለል ስፋት ያለው ፕላዛ፣
- በአንድ ጊዜ 500 መኪናዎችን ማቆም የሚችሉ ባለ ሦስት ወለል የመሬት ውስጥ ወለሎችን (Basements parking) መኪና ማቆሚያን አካትቷል።
- ዘመናዊ የፓርኪንግ ማኔጅመንት ሲስተም፣ የኤሌክትሪክ መኪና ቻርጅ ማድረጊያ ጣቢያ እና የእሳት አደጋ መከላከያ ዘዴ የተገጠመለትም ነው።
- 7 ሄክታር መሬት የሚሸፍን ውብ የአረንጓዴ ስፍራ፣ ምቹ የእግረኛ መንገዶች፣ ዘመናዊና ባህላዊ የስጦታ ዕቃ መሸጫዎች፣ ሬስቶራንቶች፣ ካፌዎች እና ቢሮዎችንም ይዟል።
- በተያያዘም 2.2 ኪሎ ሜትር ርዝመት ያለው የቁርጥሜ የወንዝ ዳርቻ ልማት ፤
- የተለያዩ የሕዝብ አገልግሎት መስጫዎችን፣ የሕፃናት የአዋቂዎች ስፖርት ማዘውተሪያዎችን አካትቶ በጽዱና በቆንጆ ሁኔታ ተገንብቷል።
- የህፃናት መጫወቻ
- የስፓርት ሜዳ
- 5 አንፊ ትያትር አካትቷል።
ስለ ከተሜነት ስናወራ የተሳለጠ መሰረተ ልማት ያለዉ ፣የህዝብ የጋራ መገልገያ ስፍራዎች ያሉት ፣ የስራ እድልን የሚፈጥር ንፁህ፣ ውብ፣ምቹ መኖሪያ እና ጤናማ አካባቢን መፍጠር ነው !
ይህ ፕሮጀክት በተቀመጠለት ጊዜና በታለመለት የጥራት ደረጃ ተጠናቆ ለአገልግሎት እንዲበቃ ላደረጋችሁ ወጣት የምህንድስና እና የአርክቴክቸር ባለሙያዎች፣ የዲዛይንና ግንባታ ቢሮ፣ የአረንጓዴና ውበት ቢሮ፣ የአዲስ አበባ መንገዶች ባለሥልጣን፣ የአዲስ አበባ ውኃና ፍሳሽ ባለሥልጣን፣ የኢትዮጵያ ኮንስትራክሽን ድርጅት፣ ቲ ኤን ቲ (TNT) ኮንስትራክሽን፣ እንዲሁም በየደረጃው ለነበራችሁ ባለሙያዎችና የጉልበት ሠራተኞች በሙሉ ላቅ ያለ ምስጋናዬን አቀርባለሁ።
ፈጣሪ ኢትዮጵያን እና ሕዝቦቿን ይባርክ!"
ከንቲባ አዳነች አቤቤ
Comments
ምንም አልተገኘም.
አስተያየቶችዎን ይተዉት.