ዛሬ ደሳሳ ቤቶችን በማንሳት የሁለት ተጨማሪ ባለ...

image description
- ውስጥ Current Affairs    0

ዛሬ ደሳሳ ቤቶችን በማንሳት የሁለት ተጨማሪ ባለ 9 ወለል (G+8) ህንፃዎች ግንባታ ለማስጀመር የመሰረተ ድንጋይ የማስቀመጥ ስራ አከናውነናል ።

አምስት ነባር ቤቶችን በማንሳት በምትካቸው የተገነባውን ዘመናዊ የመኖሪያ አፓርትመንት ቀድመው በቦታው ይኖሩ ለነበሩት  ብቻ ሳይሆን፣ በአጠቃላይ በአካባቢው በደሳሳ የቀበሌ  ቤቶች  በአስቸጋሪ ሁኔታ ውስጥ ይኖሩ የነበሩ ወገኖቻችንም በሙሉ ወደ አዲሱ ቤት በማስገባት ደሳሳ ቤቶቹን በማንሳት ሁለት ተጨማሪ ጂ+8 (G+8) ህንፃዎችን ግንባታ ለማስጀመር የመሰረተ ድንጋይ አስቀምጠናል። 

ቤት የማስተላለፊያ ስርዓቱንም በመሰረታዊ ሪፎርም ስራና አሰራሩን ግልፅ በማድረግ፣ በህዝብ ፊት ዕጣ  አውጥተን ቁልፍ በመስጠት የቤት ማስተላለፍ  አሰራር ለውጥ አምጥተናል ።

የግንባታ ወጪውን በመሸፈን አብረውን በትብብር ለመገንባት  ቃል ለገቡልን አዋሽ ባንክ እና ኤም ኤን አር ሲ (MNRC) ጥሬ እቃዎች አስመጪ እና ላኪ ድርጅት ከልብ የመነጨ ምስጋናዬን አቀርባለሁ።

ፈጣሪ ኢትዮጵያን እና ሕዝቦቿን ይባርክ !
ከንቲባ አዳነች አቤቤ


Comments

ምንም አልተገኘም.

አስተያየቶችዎን ይተዉት.