የፊታችን እሁድ የሚከበረውን የትንሳኤ በዓል በሰላም እንዲከበር ዝግጅት መደረጉን የአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር ሰላምና ፀጥታ ቢሮ አስታወቀ ።
ቢሮዉ በዓሉ በሰላም እንዲጠናቀቅና የገበያ ንግድ ቁጥጥር ለማረጋጋት ከማእከል እስከ ወረዳ ከሚገኙ የባለድርሻ አካላት ግብረሃይል ጋር ዉይይት አድርጓል፡፡
የአዲስ አበባ ከተማ ሰላምና ፀጥታ አስተዳደር ቢሮ ኃላፊ ወ/ሮ ሊዲያ ግርማ አንደተናገሩት አዲስ አበባ ከተማ ትልቁን የኢኮኖሚ እንቅስቃሴ የምታስተናግድ በመሆኗ መጪዉ የፋሲካ በዓል በሰላም እንዲጠናቀቅና የተረጋጋ የግብይት ስርዓት እንዲሰፍን ሁላችንም ልምድና ተሞክሮአችንን በሚገባ መጠቀም እንደሚገባ ገልፀዋል፡፡
ሃላፊዋ አክለዉም በአሁኑ ሰዓት በአምስቱ የመግቢያና የመዉጫ በሮች የምርት አቅርቦት እጥረት እንዳያጋጥም በቅንጅት እንደሚሰራ ገልፀዉ ምርት በመጋዘን የሚያከማቹ ህገ ወጦች ላይ ክትትልና ቁጥጥር በማድረግ ህጋዊ እርምጃ መዉስድ ይገባል ብለዋል፡፡
የገበያ ማእከላት፤የእሁድ ገበያዎች እና ሸማች ማህበራት ምርቶች ጥራታቸዉን በጠበቀ መልኩ መቅረባቸዉ፤በተቀመጠላቸዉ የዋጋ ተመን መሰረት ግብይቱ መፈፀሙንና ህጋዊ ደረሰኝ መጠቀማቸዉን ማረጋገጥና ሃሰተኛ የገንዘብ ኖቶችን የሚጠቀሙትን ላይ እርምጃ መዉሰድ እንደሚገባ የቢሮ ሃላፊዋ አሳስበዋል፡፡
በተመሳሳይም የትራፊክ ፍሰትን የሚያስተጓጉሉ ህገወጥ የጎዳና ንግዶች ላይ ተገቢዉን ክትትልና ቁጥጥር ማድረግ ከዚህ ጋር ተያይዞ የቁም ከብቶች በተወሰነላቸዉ የገበያ ቦታ ብቻ ግብይት እንዲፈፅም፤ጫኝና አዉራጆች ላይ ክትትልና ቁጥጥር እንዲደረግ ገልፀዉ በከተማችን በዓሉ ያለምንም የፀጥታ ችግር እንዲከበር የፀጥታ አካሉ፤የሰላም ሰራዊቱ፤ከማእከል እስከ ወረዳ ያለዉ ግብረ ሃል ከህዝባችን ጋር በቅንጅት እንዲሰራ በማለት የስራ መመሪያ ሰጥተዋል፡፡
የዉይይቱ ተሳታፊዎች በበኩላቸዉ ቅድመ ዝግጅት ስራዉን በተደራጀ አግባብ እስከ ታች እየተሰራ መሆኑን ገልፀዉ ይህን ይበልጥ በማጠናከር ህዝባችን በኣሉን በሰላም እንዲያሳልፍ ሃያ አራት ሰኣት ተግተን እንሰራለን ብለዋል፡፡
Comments
ምንም አልተገኘም.
አስተያየቶችዎን ይተዉት.