በደቡብ ኢትዮጵያ ክልል በጋሞ ዞን በተለያዩ አካባቢዎች በተከሰተው የመሬት መንሸራተት እና የጎርፍ አደጋ በወገኖቻችን ላይ በደረሰው ጉዳት የተሰማኝን ጥልቅ ሀዘን እገልጻለሁ።
በአደጋው ለተጎዱ ቤተሰቦች፣ ለወዳጅ ዘመዶቻቸውና ለመላው የክልሉ ህዝብ ልባዊ መጽናናትን እመኛለሁ።
በቀጣይም በአደጋው የተጎዱ ወገኖቻችንን መልሶ ለማቋቋም በሚደረገው ጥረት ሁሉ፣ የአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር እና ሕዝብ ከጎናችሁ የሚቆም መሆኑን አረጋግጣለሁ።
ፈጣሪ ኢትዮጵያን እና ህዝቦቿን ይባርክ!
ከንቲባ አዳነች አቤቤ
Comments
ምንም አልተገኘም.
አስተያየቶችዎን ይተዉት.