ዛሬ ማለዳ 2ኛው ከተማ አቀፍ የአዲስ አበባ ፖሊስ ስፖርት ውድድርና ፌስቲቫል በድምቀት ተጀምሯል።
"ተልዕኮን በጀግንነት፣ ስፖርትን በውጤት" በሚል መሪ ቃል የሚካሄደው 2ኛው ከተማ አቀፍ የአዲስ አበባ ፖሊስ ስፖርት ውድድርና ፌስቲቫል ዛሬ በአበበ ቢቂላ ስታድየም በድምቀት ተጀምሯል። በስድስት የስፖርት አይነቶች የሚካሄደው ይህ ውድድር፣ ከዛሬ ጀምሮ ለሚቀጥሉት ሁለት ሳምንታት በከተማዋ በሚገኙ የተለያዩ የስፖርት ማዘውተሪያ ስፍራዎች የሚቀጥል ይሆናል ።
የፖሊስ ሰራዊት ከሰላም ጥበቃ ተልዕኮው ጎን ለጎን፣ የሀገርን ስም የሚያስጠሩና ሰንደቅ ዓላማን በዓለም አቀፍ መድረኮች ከፍ የሚያደርጉ ዝነኛ ስፖርተኞችን በማፍራት ረገድ የማይተካ ሚና እያበረከተ ይገኛል፣ ይህ ተሳትፎ በቀጣይም ተጠናክሮ ሊቀጥል ይገባል ።
ፈጣሪ ኢትዮጵያን እና ሕዝቦቿን ይባርክ !
ከንቲባ አዳነች አቤቤ
Comments
ምንም አልተገኘም.
አስተያየቶችዎን ይተዉት.