ከንቲባ አዳነች አቤቤ ለከተማችን ነዋሪዎች ያስተ...

image description
- ውስጥ Current Affairs    0

ከንቲባ አዳነች አቤቤ ለከተማችን ነዋሪዎች ያስተላለፉት መልክት

ለከተማችን ነዋሪዎች በሙሉ!

በአሁኑ ወቅት በመካከለኛው ምሥራቅ በተፈጠረው ቀውስ ምክንያት፣ ሀገራችንን ጨምሮ  ነዳጅ ገዝተው የሚጠቀሙ ሀገራት አቅርቦቱን እንደልብ ለማግኘት ተቸግረዋል። 

በመሆኑም፣ ችግሩ ተፈትቶ ወደ መደበኛው የነዳጅ አቅርቦት ሥርዓት እስክንመለስ ድረስ ነዳጅን በቁጠባ መጠቀም ይኖርብናል።

ስለሆነም የከተማችን ነዋሪዎች አጫጭር መንገዶችን በእግር በመጓዝ፣ እንዲሁም የብስክሌት አማራጮችን እና የኤሌክትሪክ ተሽከርካሪዎችን በመጠቀም እንድትተባበሩ ጥሪያችንን እናስተላልፋለን።

ፈጣሪ ኢትዮጵያን እና ህዝቦቿን ይባርክ!
ከንቲባ አዳነች አቤቤ


Comments

ምንም አልተገኘም.

አስተያየቶችዎን ይተዉት.