ቤጄአይ ኢትዮጵያ ለጤና ጎጅ የሆነ አደገኛ ኬሚካ...

image description
- ውስጥ Current Affairs    0

ቤጄአይ ኢትዮጵያ ለጤና ጎጅ የሆነ አደገኛ ኬሚካል ወደ ወንዝ በመልቀቁ 2 ሚሊዮን ብር ተቀጣ

የአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር  ደንብ ማስከበር ባለስልጣን  በልደታ ክፍለ ከተማ ጽ/ቤቱ ከአካባቢ ጥበቃ  ባለስልጣን ጋር  በጋራ በመሆን በልደታ ክፍለ ከተማ ቤጄአይ ኢትዮጵያ ለጤና ጎጅ የሆነ አደገኛ ኬሚካል ወደ ወንዝ በመልቀቁ ከዚህ በፊት የተቀጣ በመሆኑ በሪከርድ 2,000,000/ሁለት ሚሊዮን/ ብር መቅጣቱ ገለፀ።

ቅጣቱ የተካሄደው በልደታ ክፍለ ከተማ ወረዳ 9 ልዩ ቦታ ተግባረዕድ አካባቢ ብክለቱ በአካባቢ ጥበቃ ባለስልጣን ባለሙያዎች አደገኛና ለጤና ጎጂ ኬሚካል መኖሩ በላብራቶሪ ናሙና ተወስዶ የተረጋገጠ ሲሆን በደንብ ቁጥር 180/2017 መሰረት በሪከርድ 2,000,000 ብር መቀጣቱ ተገልጿል ።

ባለስልጣኑ በተደጋጋሚ በተለያዩ አማራጮች የግንዛቤ ፈጠራ ስራ እየሰራ ቢሆንም ከህገ ወጥ ተግባራቸው በተሰጣቸው ግንዛቤና ማስጠንቀቂያ መሠረት ማስተካከያ በማያደርጉ ግለሰቦች እና ድርጅቶች ላይ የሚወስደው አስተዳደር እርምጃ  አጠናክሮ እንደሚቀጥል አስታውቋል።

የከተማው ነዋሪዎች በሚኖርበት አካባቢ ህገወጥ ተግባራትን ሲከናወኑ  ካስተዋሉ በነፃ የስልክ መስመር 9995 ጥቆማ እንዲሰጡ ባለስልጣኑ መስሪያ ቤቱ ጥሪውን አስተላልፎዋል።

የአዲስ አበባ ደንብ ማስከበር ባለስልጣን


Comments

ምንም አልተገኘም.

አስተያየቶችዎን ይተዉት.