በድብደባ ወንጀል ጠርጥሬያቸዋለሁ ያላቸውን የጸጥታ እና የአስተዳደር አካላትን በቁጥጥር ስር አውሎ ምርመራ እያጣራ መሆኑን የአዲስ አበባ ፖሊስ ጠቅላይ መምሪያ አስታወቀ።
ድርጊቱ የተፈፀመው የካቲት 27 ቀን 2018 ዓ/ም ከምሽቱ 3፡30 ሠአት በንፋ ስልክ ላፍቶ ክፍለ ከተማ ወረዳ 05 ልዩ ቦታው ካባ ጉሊት እየተባለ ከሚጠራው አካባቢ ነው።
ወ/ሮ እናት አበበ በመኖሪያ ቤታቸው አረቄ በመሸጥ የሚተዳደሩ ሲሆኑ በዕለቱ በአካባቢው በወንጀል መከላከል ስራ ላይ ተሰማርተው የነበሩ የፖሊስ አባላት እና የወረዳ 5 አስተዳደር አመራሮች ወደ ግለሰቧ መኖሩያ ቤት በመግባት “አረቄ እዚህ መሸጥ የለበትም “ በሚል በተፈጠረ አለመግባባት የግል ተበዳይ ላይ ጉዳት ከመድረሱም ባሻገር ለንግድ የተቀመጠ ወደ 60 ሊትር የሃበሻ አረቄ እንዲደፋ ይደረጋል፤ በዚህ ምክንያት የተፈጠረውን ፀብ መነሻ አድርጎ
የወ/ሮ እናት አበበ ልጅ የሆነው ናትናኤል ገመዳ እናቴ እግሯ ላይ እና ሌላ አካሏ ላይ ጉዳት ደርሶባታል በተጨማሪም 60 ሌትር አረቄ ደፍተውብናል፤ በሚል በራሱ ቲክቶክ ፕላት ፎርም ላይ ተንቀሳቃሸ ምስል በማጋራቱ ፖሊስ የተለቀቀውን ተንቀሳቃሸ ምስል መነሻ በማድረግ ባደረገው ማጣራት በድብደባ ወንጀል ጠርጥሬያቸዋለሁ ያላቸውን ሁለት የፖሊስ አባላትና ሦስት የወረዳውን አመራሮች በቁጥጥር ስር አውሎ ምርመራ እያጣራ መሆኑን የአዲስ አበባ ፖሊስ ጠቅላይ መምሪያ ገልጿል።
Comments
ምንም አልተገኘም.
አስተያየቶችዎን ይተዉት.