"በመዲናችን አዲስ አበባ የተከናወነወና እየተከናወነ ያለዉ የኮሪደር ልማት ድርብርብ ግቦችን ሰንቆ ዘርፈ-ብዙ ስኬቶች የተረጋገጡበት ነዉ፡፡"ጠ/ሚ/ር አብይ አህመድ (ዶ/ር)
በማክሮ ኢኮኖሚ ስብራት የተቀመጠዉን ስራ አጥነት ኮሪደር ልማቱ እየተሰራ ብቻ ሳይሆን ካለቀም በኋላ ለዜጎች የስራ እድል በመፍጠር ስብራቱን በመጠገን አበርክቶዉ የጎላ ነዉ ሲሉ ጠ/ሚ/ር አብይ አህመድ (ዶ/ር) ገልፀዋል፡፡
ወጣቶች የትምህርት ተቋማት ገብተዉ ከሚያገኙት እዉቀት በላቀ የተግባር እዉቀት በመጨበጥ በሌሎች ክልል ከተሞች ሳይቀር ፈጠራ ጭምር የታከለበት አስደማሚ ሀገር-በቀል እዉቀቶች እዉን መሆናቸዉን ተናግረዋል፡፡
በከተማዋ ዋና ችግር የሆነዉን የቤት አቅርቦት እጥረትን ለመፍታት የኮሪደር ልማት አንዱ አካል በማድረግ በመቶ ሺህ የሚቆጠሩ ቤቶችን በአጭር ጊዜ በፍጥነትና በጥራት በመገንባት ዜጎች ፍትሃዊ የቤት ተጠቃሚ መሆን የቻሉበት ነዉ ብለዋል፡፡
አክለዉም ፖርኪንጎች እና ተርሚናሎች፣የእግረኛ እና የሳይክል መንገዶች፤የኤሌትሪክ መኪና ቻርጅ ማድረጊያዎች፤የመንገድ ላይ ካሜራዎች የትራንስፖርት ሲስተሙን ይበልጥ የሚያሳልጡ የመዲናችን የስማርት ትራንስፖርት ሌለኛዉ የኮሪደር ልማት የእሳቤ ዉጤቶች ናቸዉ ሲሉም ገልፀዋል፡፡
ከማህበራዊ ግብ አንፃር የኑሮ ደረጃን ለማሻሻል በተሰጠዉ ልዩ ትኩረት ተደራሽነት፤አካታችነት እና ሳቢነት የተተገበሩበት፤ንፅህናዉ የተጠበቀ ዘላቂ ስነ-ምህዳር በመፍጠር ካባቢያዊ አየር ንብረት ጥበቃ የተረጋገጠበት ፤ከተማ ብቻ ሳይሆን ባህል እና ትዉልድ የተቀየረበት በጥቅሉ ከተማዋ ከስም ባለፈ በተግባር ስሟን ያስመሰከረችበት፤ታሪካዊ መገለጫዋ ጭምር መሆኑን ጠቁመዋል፡፡
በመጨረሻም -አዲስ አበባን ማእከል አድርጎ የተጀመረዉ ኮሪደር ልማት አዲስ አበባ በእንድ በኩል የብልፅግና ማሳያ ምልክት በሌላ በኩል ደግሞ የቱሪዝም መዳረሻ እና መተላለፊያ ተመራጭ መሆኗንና ለነዋሪዎቿ ብቻ ሳይሆን ለዉስጥም ሆነ ለዉጪዉ ልምድ የሚቀሰምባት ከተማ ነች ሲሉ ጠ/ሚ/ር አብይ አህመድ (ዶ/ር) በሰጡት ማብራሪያ እና ምላሽ ገልፀዋል፡፡
Comments
ምንም አልተገኘም.
አስተያየቶችዎን ይተዉት.