በአዲስ አበባ ከተማ የትንሳዔ በዓልን በማስመልከት የቀረቡ ምርቶች ህብረተሰቡን ፍላጎት በማሟላት እና የዋጋ ንረትን በመከላከል በሚያስችል ሁኔታ በቂ ምርት እየቀረበ ይገኛል። የህብረት ስራ ኮሚሽነር ወ/ሮ ልዕልቲ ግደይ
የፊታችን እሁድ በክርስትና እምነት ተከታዮች ዘንድ የሚከበረው የትንሳዔ በዓል ላይ የምርት እጥረት እንዳያጋጥም በቂ ዝግጅት መደረጉን እና አቅርቦቱም ለህብረተሰቡ በሚያመች መልኩ በየአካባቢው በቅንጅት የቀረበ መሆኑን ገልፀዋል።
በምርት ጥራት አቅርቦት ፣ በዋጋ ተመጣጣኝነት እና ለህብረተሰብ አገልግሎት እየተሰጠ መሆኑን በዛሬው ዕለት ተዘዋውረን ለመመልከት ችለናል።
በተለያዩ ቦታዎች ተዘዋውረን እንደተመለከት ነው የግብርና ምርቶች ፤ የእንስሳት ምርት ፣በእሁድ ገቢያዎች፤ በሸማች ማህበራት ፣በባዛርና ኤግዚቢሽኖች ምርቶች በሬ፣ በግ፣ ዶሮ፣እንቁላል፣ጤፍ፣ዱቄት ፣ቅቤና አይብን ጨምሮ የተለያዩ የግብርናና የኢንዱስትሪ ምርቶች ተዘጋጅተው በ11ም ክ/ከተማ ና በሁሉም ወረዳዎች በስፋት እና በአይነት ቀርበዋል።
በዓል ምክንያት በማድረግ በቂ ምርት እንዲኖርና ከማድረግ በተጨማሪ የዋጋ ንረት እንዳይኖረው ለማስቻል በከተማ አስተዳደሩ በኩል ጥብቅ ክትትል እንደሚደረግም ኮሚሽነሯ ተናግረዋል።
የተለያዩ የግብይት ማዕከላት ምርቶችን በሰፊዉ ከማቅረብ ስራ ጎን ለጎን የዋጋ ንረት እንዳይፈጠር ቅንጅታዊ የክትትልና የቁጥጥር ስራዉ ተጠናክሮ ይቀጥላልም ተብሏል።
Comments
ምንም አልተገኘም.
አስተያየቶችዎን ይተዉት.