ለዓለማቀፍ ኮንፈረንሶች ተመራጭ መሆኗን በተግባር...

image description
- ውስጥ Current Affairs    0

ለዓለማቀፍ ኮንፈረንሶች ተመራጭ መሆኗን በተግባር እያረጋገጠች ያለች ስሉጥ ከተማ (Smart-City)፥ አዲስ አበባ!

አዲስ አበባ “5ኛውን ዓለም አቀፍ የአፍሪካ የሕዝብ ጤና ጉባኤን” እንድታስተናግድ ተመረጠች። 
 
የዓለም አቀፍ ዲፕሎማሲ መዲና ውቧ አዲስ አበባ፣ ለዓለም አቀፍ ጉባኤዎች ተመራጭ መዳረሻ መሆኗን በተግባር  እያረጋገጠች ነው። 

ኢትዮጵያ ያላትን ጠንካራ የማስተናገድ አቅም እና ልዩ የእንግዳ ተቀባይነት ባህል ከግምት ውስጥ በማስገባት፣ የአፍሪካ የበሽታ መቆጣጠሪያ እና መከላከል ማዕከል (Africa CDC) ይህንን ትልቅ ዓለም አቀፍ ስብሰባ በአዲስ አበባ እንዲካሄድ መርጧል።

በዚህ ጉባኤ ላይ ከ30,000 በላይ ተሳታፊዎች በአካል ይገኛሉ ተብሎ እንደሚጠበቅ ከኢፌዴሪ የውጭ ጉዳይ ሚኒስቴር የተገኘው መረጃ ያመለክታል።


Comments

ምንም አልተገኘም.

አስተያየቶችዎን ይተዉት.