የትንሳዔ በዓል ሰላማዊነትና ድምቀት ዙሪያ ከሰላም ሰራዊት አባላት ጋር ውይይት ተደረገ::
የፊታችን እሁድ የትንሳዔ በዓል ያለምንም የፀጥታ ችግር በሰላም ተከብሮ እንዲውል የአዲስ አበባ ከተማ ሰላምና ፀጥታ አስተዳደር ቢሮ ከ11ዱም ክፍለ ከተሞች ከተወጣጡ የሰላም ሰራዊት አባላት ጋር ውይይት አድርጓል፡፡
የአዲስ አበባ ከተማ የሰላምና ፀጥታ አስተዳደር ቢሮ ሃላፊ ወ/ሮ ሊዲያ ግርማ በመድረኩ እንዳሉት የሰላም ሰራዊት 24 ሰዓት ከፀጥታ መዋቀሩ ጋር በቅንጅትና በቁርጠኝነት በመስራቱ በከተማችን ሰላምና ደህንነት በዘላቂነት እንዲጠበቅ በማድረግ የሰላም ባለቤትነቱን አረጋግጧል ብለዋል፡፡
ሃላፊዋ አክለውም ከፊታችን እሁድ የሚከበረውን በዓሉን ሽፋን በማድረግ በገበያ ቦታዎችና ህዝብ በሚበዛባቸው አካባቢዎች ሁከትና ስጋት እንዳይፈጠር የነበሩን ልምድና ተሞክሮ በመጠቀም የከተማችንን ዘላቂ ሰላም ማፅናት ይጠበቅብናል ብለዋል፡፡
የአዲስ አበባ ከተማ ሰላምና ፀጥታ አስተፈዳደር ም/ቢሮ ሃላፊ አቶ ሚደቅሳ ከበደ በበኩላቸው በበጀት ዐመቱ የስኬታችን ቁልፍ ያሏቸው ህዝቡን የሰላም ባለቤት በማድረግ፤ ጠንካራ ስምሪት በመስጠት እና 24 ሰዓት ተደራጅተን በቅንጅት በመስራታችን ነው ብለዋል::
የትንሳዔ በዓልን ስናከብርም በዚሁ አግባብ በገበያ ቦታዎች፤ በአደባባይ ቦታዎች እና የስጋትና የወንጀል አካባቢዎችን በመለየት የፀረ ሽብርተኞችን ሴራ ለማክሸፍ ከአጎራባቾቻችን ጋር እጅና ጓንት ሆነን መስራት ይገባል ብለዋል፡፡
Comments
ምንም አልተገኘም.
አስተያየቶችዎን ይተዉት.