በመካከለኛው ምስራቅ ያለው ጦርነት ያስከተለውን...

image description
- ውስጥ Current Affairs    0

በመካከለኛው ምስራቅ ያለው ጦርነት ያስከተለውን ዓለም አቀፋዊ የነዳጅ አቅርቦት ችግር በሀገር ደረጃ ለመቋቋም ከተማ አስተዳደሩ የተለያዩ አሰራሮችን በመተግበር ላይ እንደሚገኝ ተገለጸ።

ለችግሩ የተደራጀ አመራር ለመስጠት ሲባል በሀገር ደረጃ የተዋቀረውን አደረጃጀት ተከትሎ የከተማ አስተዳደሩ በምክትል ከንቲባው የሚመራ የራሱን ግብረ ኃይል በመፍጠር ወደ ስራ የገባ ሲሆን ይሄው ግብረ ኃይልም በዛሬው እለት ሁለት መድረኮችን በማዘጋጀት ሰፊ ምክክር አድርጓል። 

‎በመድረኩም የካፒታል ፕሮጀክት የሚመሩ ተቋማት የቅድሚያ ቅድሚያ የሚሰጧቸውን ፕሮጀክቶች እንዲለዩና ከተቋራጮች ጋር እንዲወያዩ ከመደረጉም ባለፈ የግንዛቤ ፈጠራን፣ የተሽከርካሪ ስምሪትን እንዲሁም የነዳጅ አጠቃቀምና ቁጥጥርን መሰረት ያደረጉ ውይይቶች ተካሂደዋል።

‎ግብረ ኃይሉ የፌደራሉን አቅጣጫ በማክበር ለህብረተሰቡ አንገብጋቢ ለሆኑ አገልግሎቶች ቅድሚያ የነዳጅ አቅርቦት የሚገኝበትን አሰራር በመወያየት ውሳኔ ያሳለፈ ሲሆን በመጨረሻም የከተማዋ ምክትል ከንቲባ እና የኢንዱስትሪ ልማት ቢሮ ኃላፊ ክቡር አቶ ጃንጥራር አባይ አቅጣጫ አስቀምጠዋል። 

‎በዚህም መሰረት የግንዛቤ ፈጠራ ስራው በትራንስፖርት፣ በፋይናንስና በፀጥታ ተቋማት በኩል ተጠናክሮ እንዲቀጥል እንዲሁም የትራፊክ ማኔጅመንትና ትራፊክ ፖሊስ ሰዓት በመከፋፈልና በመመደብ ረጅሙን ሰልፍ እንዲያስተካክሉ አቅጣጫ ተቀምጧል። 

‎በተጨማሪም በየማደያው የመረጃ ተደራሽነት እንዲኖር የከተማው ኢኖቬሽንና ቴክኖሎጂ ቢሮ ከፖሊስ ጋር በመቀናጀት አሰራር እንዲዘረጋና ሚዲያዎችም እንደየተቋማቱ ባህሪ መረጃ ለህብረተሰቡ እንዲያደርሱ አቅጣጫ ተሰጥቷል።

 


Comments

ምንም አልተገኘም.

አስተያየቶችዎን ይተዉት.