የኢፌዲሪ ፕሬዝዳንት ሳህለወርቅ ዘውዴ መጪውን የ...

image description
- ውስጥ Current Affairs    0

የኢፌዲሪ ፕሬዝዳንት ሳህለወርቅ ዘውዴ መጪውን የፋሲካ በዓል ምክንያት በማድረግ በአራዳ ክ/ከተማ በመገኘት ማዕድ አጋርተዋል::

የኢፌዲሪ ፕሬዝዳንት ሳህለወርቅ ዘውዴ ማዕድ ያጋሩት በመጪው እሁድ የሚከበረውን የፋሲካ በዓል ምክንያት በማድረግ በአራዳ ክ/ከተማ ወረዳ 8 በተዘጋጀው የማዕድ ማጋራት መርሃ ግብር ላይ ነው፡፡ 

በመርሃ ግብሩ ላይ የኢፌዲሪ ፕሬዝዳንት ክብርት ሳህለወርቅ ዘውዴን ጨምሮ የአራዳ ክ/ከተማ ዋና ስራ አስፈጻሚ ወ/ሮ መቅደስ ተስፋዬ እና ሌሎች አመራሮች የተገኙ ሲሆን የመደጋገፍና የመረዳዳት ተምሳሌትነትን አጉልቶ በሚያሳይ መልኩ ለአቅመ ደካሞች ማዕድ ማጋራት ስነ ስርዓት ተካሂዷል፡፡ 

ለአቅመ ደካሞች ካጋሩት ማዕድ በተጨማሪ ለመከላከያ ሰራዊት አባላት ለበዓል መዋያ የሚሆን የበግ ስጦታ አበርክተው በዓሉ የሠላምና የጤና እንዲሆን መልካም ምኞታቸውን ገልፀዋል፡፡


Comments

ምንም አልተገኘም.

አስተያየቶችዎን ይተዉት.