አዲስ አበባ የዓለም አቀፉን የብስክሌት ውድድር (UCI City Mountain Bike Eliminator) ልታስተናግድ ነው ።
የዓለም አቀፉ የብስክሌት ህብረት (UCI) ዕውቅና የሰጠውና በዓለም አቀፍ ደረጃ ከፍተኛ ተወዳጅነት ያለው "ሲቲ ማውንቴን ባይክ ኤሊሚኔተር ፕሮ ሊግ" በአፍሪካ ለመጀመሪያ ጊዜ በኢትዮጵያ፣ አዲስ አበባ ሊካሄድ መሆኑ ታወቀ።
ውድድሩ በመጪው ሚያዝያ 25 ቀን 2018 ዓ.ም በፒያሳ አድዋ ድል መታሰቢያ ሙዚየም ዙሪያ ይካሄዳል። ከ24 የአውሮፓ እና ከ10 የአፍሪካ ሀገራት የተወጣጡ ከ60 እስከ 80 የሚደርሱ ምርጥ ብስክሌተኞች በውድድሩ ላይ ይሳተፋሉ።
ዉድድሩ ለዓለም አቀፉ የቴሌቪዥን ጣቢያዎች በቀጥታ የሚተላለፍ ሲሆን፣ ከ20 ሚሊዮን በላይ ተመካቾች ይከታተሉታል ተብሎ ይጠበቃል።
Comments
ምንም አልተገኘም.
አስተያየቶችዎን ይተዉት.