ከንቲባ አዳነች አቤቤ የአዲስ ስፖርት ፓርክ ግንባታ ፕሮጀክት በተለወጠ የሥራ ባህል እንዲጠናቀቅ ላደረጉ አካላት ምስጋና አቀረቡ።
በክቡር ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ (ዶ/ር) እና ከንቲባ አዳነች አቤቤ ተመርቆ ለሕዝብ ክፍት በሆነውና በዓይነቱ የመጀመሪያ በሆነው የአዲስ ስፖርት ፓርክ ግንባታ ሂደት ላይ ለተሳተፉ፣ እንዲሁም ፕሮጀክቱን በተለወጠ የ24/7 የሥራ ባህል ሌትና ቀን በመሥራት በስኬት እንዲጠናቀቅ ላስቻሉ አካላት ምስጋና አቅርበዋል።
"የአዲስ አበባ አስደናቂ የልማት ጉዞ በስኬት ይቀጥላል" ያሉት ከንቲባ አዳነች አቤቤ፤ ከተማዋ ሁልጊዜም ሕዝብን ተጠቃሚ ባደረጉ አዳዲስ ልማቶች ትደምቃለች ብለዋል።
አዲስ አበባችንን በዓለም አቀፍ ደረጃ ይበልጥ ተወዳዳሪ፣ ለነዋሪዎቿ ምቹ እና ለጎብኚዎች ተመራጭ ውብ ከተማ የማድረግ ጉዟችን ተጠናክሮ ይቀጥላል ሲሉም ገልጸዋል።
የከተማ አስተዳደሩ ካቢኔ አባላት እና ከፍተኛ አመራሮች በአስደናቂ ፍጥነት የተጠናቀቀውን የአዲስ ስፖርት ፓርክ መሠረተ ልማቶች ጎብኝተዋል።
ለተጨማሪ የመረጃ አማራጮች
https://linktr.ee/addisababacommunication
Comments
ምንም አልተገኘም.
አስተያየቶችዎን ይተዉት.