የአዲስ አበባ ብልፅግና ፓርቲ ጽ/ቤት ኃላፊ አቶ...

image description
- ውስጥ Current Affairs    0

የአዲስ አበባ ብልፅግና ፓርቲ ጽ/ቤት ኃላፊ አቶ ሞገስ ባልቻ የትንሳዔ በዓልን ምክንያት በማድረግ በቂርቆስ ክፍለ ከተማ በመገኘት ማዕድ አጋርተዋል፡፡

የዛሬው እለት በአዲስ አበባ ከተማ ቂርቆስ ክ/ከተማ በተካሄደው መርሃ ግብር ከ19 ሺህ በላይ የሆኑ ክፍለ ከተማ ነዋሪ የሆኑ አቅመ ደካማ ዜጎች ተሳትፈውበታል።

አቶ ሞገስ ባልቻ ማዕዱን ባጋሩበት ወቅት እንዳሉት ሀገራችን በርካታ አስተሳሳሪ ማህበራዊ መሰረትና እሴት ያላት ሀገር መሆኗን የምንጋራቸው ማዕዶች ምስክሮቻችን ናቸው ብለዋል፡፡

እንደ ከተማ አስተዳደር በዛሬው እለት ብቻ ከ250 ሺ በላይ ነዋሪዎች ማዕድ መጋራታቸውን ያስታወሱት አቶ ሞገስ ይህ ትልቅ እሴት ከአዲስ አበባ ቢጀመርም ወደሌሎች ክልሎችም እየሰፋ መጥቷልና በቀጣይ ይበልጥ አጎልብተነው ወደ ብልፅግና ከፍታችን መውጣታችንን እንቀጥላለን ብለዋል። 

የቂርቆስ ክፍለ ከተማ ዋና ስራ አስፈፃሚ አቶ ሙባረክ ከማል በበኩላቸው ብልፅግና ፓርቲ ሰው ተኮር ፓርቲ ነው ስንል በዓላትን ከህዝቡ ጋር እንዲህ ተካፍሎ ማሳለፉ አንዱ ማሳያ መሆኑን ጠቅሰው በዛሬው እለት ብቻ በሁሉም ወረዳዎች ከ19 ሺህ በላይ ነዋሪዎችን ማዕድ አጋርተናል ብለዋል።

የዛሬው ማዕድ ማጋራት አካል ጉዳተኞችን፣ ህሙማንና በእድሜ የገፉ ነዋሪዎችን፣ ዝቅተኛ ደሞዝ ያላቸው የመንግስት ሰራተኞችንና ሌሎች የህብረተሰብ ክፍሎችን ያካተተ ነው፡፡


Comments

ምንም አልተገኘም.

አስተያየቶችዎን ይተዉት.