የዋጋ ንረትን ለማረጋጋት የሚረዱ የገቢያ ማዕከላ...

image description
- ውስጥ Current Affairs    0

የዋጋ ንረትን ለማረጋጋት የሚረዱ የገቢያ ማዕከላት በአዲስ አበባ!

የአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር በአምስቱም የከተማይቱ መግቢያ በሮች የመሰረታዊ ሸቀጦችን የዋጋ ንረት ለማረጋጋት የሚረዱ የግብርና ምርቶች መሸጫ ገቢያ ማዕከላት ገንብቶ ለአገልግሎት አውሏል፡፡ ማዕከላቱ በላፍቶ ቁጥር1 እና 2፣አቃቂ ቃሊቲ፣  ለሚ ኩራ እና ኮልፌ ክፍለ  ከተሞች የተገነቡ እና ከፍተኛ ኢኮኖሚያዊና ማህበራዊ ፋይዳ ያላቸው ናችው፡፡ 

ከተማ አስተዳደሩ በከተማዋ ያለውን የኑሮ ውድነትና ጫና ከግምት ውስጥ በማስገባት ችግሩን ለማስቀረትና ገበያውን ለማረጋጋት ከወሰዳቸው ዘርፈ ብዙ እርምጃዎች መካከል ግንባር ቀደም እና ለነዋሪው ትልቅ እፎይታን የሰጠ ተግባር ነው፡፡ 

በነዚህ የገቢያ ማዕከላት በሌማት ትሩፋትና በከተማ ግብርና ምርታማነትን በማሳደግ ህብረተሰቡ ከሸማችነት ወደ አምራችነት እንዲሸጋገር ምቹ ሁኔታዎችን መፍጠር ተችሏል፡፡ 

በዚህም ህገወጥ ንግድና ደላላን በማስቀረት የመሰረታዊ ሸቀጦችን የዋጋ ንረት ለማረጋጋት የሚረዱ የግብርና ምርቶች በገበያ ማዕከላቱ በስፋት እንዲሰራጩ አስችሏል፡፡


Comments

ምንም አልተገኘም.

አስተያየቶችዎን ይተዉት.