በልደታ ክ/ከተማ የፋሲካ በዓልን ምክንያት በማድረግ ለ18 ሺ 600 ዜጎች ማዕድ ተጋራ
በአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር ልደታ ክ/ከተማ የፋሲካ በዓልን ምክንያት በማድረግ ለ18 ሺ 600 ባለይ ዜጎች ማዕድ የማጋራት መርሃ ግብር ተካሄደ፡፡
በማዕድ ማጋራቱ ተገኝተው ንግግር ያደረጉት በምክትል ከንቲባ ማዕረግ የአዲስ አበባ ከተማ የከተማ ውበትና አረንጓዴ ልማት ቢሮ ኃላፊ ዶክተር ጀማሉ ጀንበር እንዳሉት መተባበር መደጋገፍና የዜጎችን ችግር ተረድቶ መፍታት የለውጡ መንግስት መለያ ነው፡፡
መንግስት ሰው ተኮር ተግባርን በፕሮግራም በመቅረፅ የዜጎችን ማህበራዊና ኢኮኖሚያዊ ችግር እየፈታ ነው ያሉት ሀላፊው በተሰራው ስራም በርካታ ዜጎች ተጠቃሚ ሆነዋል ሲሉ ተናግረዋል።
በዓሉን ተደስተው እንዲውሉ በከተማችን አዲስ አበባ ብቻ ከ255 ሺ በላይ ለሚሆኑ ዜጎች በዛሬው እለት ማዕድ ይጋራል ያሉት ዶ/ር ጀማሉ ይህ ተግባር መረዳዳት፣ መደጋገፍና አብሮነታችን፣ ወንድማማችነት እንዲጎለብት ያደረገ በመሆኑ በዚህ በጎ ተግባር ለተሳተፉ ተቋማትና ባለሀብቶችም ምስጋና አቅርበዋል።
የልደታ ክ/ከተማ ዋና ስራ አስፈፃሚ አቶ ሰዒድ ዓሊ በበኩላቸው ቅን ልብ ያላቸውን ባለሀብቶች በማስተባበር በክ/ከተማች ከ18 ሺህ 600 በላይ ለሚሆኑ የሀገር ባለውለታዎች ዝቅተኛ ገቢ ላላቸው ዜጎች ማዕድ መጋራቱን ጠቅሰው አቅም የሌላቸው ዜጎች በዓሉን ተደስተው እንዲውሉ የማድረግ በህል ተጠናክሮ ይቀጥላል ብለዋል።
Comments
ምንም አልተገኘም.
አስተያየቶችዎን ይተዉት.