በየካ ክፍለ ከተማ የትንሳኤ በዓልን ምክንያት...

image description
- ውስጥ Current Affairs    0

በየካ ክፍለ ከተማ የትንሳኤ በዓልን ምክንያት በማድረግ ከ27 ሺህ በላይ ለሚሆኑ አቅመ ደካማ፣ የሀገር ባለውለታ ዜጎች መዓድ ተጋራ

በአዲስ አበባ ከተማ የካ ክ/ ከተማ በተካሄደው የማእድ ማጋራት ፕሮግራም ምክትል ከንቲባንአቶ ጃንጥራር አባይ ፣ የየካ ክ/ከተማ ዋና ስራ አስፈፃሚ አቶ ብርሀኑ ረታን ጨምሮ የክ/ከተማ እና የወረዳ አመራሮች እና ድጋፍ የተደረገላቸው የክ/ከተማው ነዋሪዎች ተገኝተዋል፡፡

የአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር ምክትል ከንቲባ አቶ ጃንጥራር አባይ ፕሮግራሙ እንዲሳካ አስተዋፅኦ ላደረጉ ልበ ቀና ኢትዮጵያዊያን ምስጋና ያቀረቡ ሲሆን በዛሬው ዕለት በደጋግ እና ልበ ቀና በጎ አድራጊዎች በከተማ ደረጃ ከ 250,000 በላይ በከተማችን ለሚገኙ አቅመ ደካሞች ማእድ የማጋራት ትልቅ ነገር ነው ብለዋል፡፡

አቶ ጃንጥራር አያይዘውም ያለንን አብሮ ተካፍሎ መብላት እና በዓል በጋራ በፍቅር ማክበር ከጥንት ጀምሮ የመጣ ኢትዬጵያዊ ባህላችን ነው: ይህ ውብ ባህላችን ዛሬም ቀጥሎ ያለንን በመካፈል በዓላትን እያከበርን እንገኛለን ብለዋል::

 መጪው የትንሳኤ በአል የሰላም፣ የጤና፣ የመተሳሰብ እንዲሆን መልካም ምኞታቸውንም ገልፀዋል፡፡ 

የየካ ክ/ከተማ ዋና ስራ አስፈፃሚ አቶ ብርሀኑ ረታ በበኩላቸው ክ/ከተማው በየጊዜው ከሚከናውናቸው ሰው ተኮር ተግባራት መካከል አንዱ የሆነውንo የማእድ ማጋራት ፕሮግራም በዚህ መልኩ ስኬታማ እንዲሆን አስዋፅኦ ላደረጉ በሙሉ ምስጋናቸውን አቅርበዋል፡፡

በክፍለ ከተማ አስተዳደሩ ግቢ ብቻ ከ2000 በላይ አቅመ ደካማ ነዋሪዎች የማእድ ማጋራት የተከናወነ ሲሆን በአጠቃላይ እንደ የካ ክ/ከተማ ከ 27,000 በላይ ለሚሆኑ አቅመ ደካማ ነዋሪዎች መጪውን የፋሲካ በአል ምክንያት በማድረግ የማእድ ማጋራት ፕሮግራም እንደተከናወነም ተገልፃል፡፡


Comments

ምንም አልተገኘም.

አስተያየቶችዎን ይተዉት.