በአዲስ አበባ ከተማ የትንሳዔን በዓል ምክንያት...

image description
- ውስጥ Current Affairs    0

በአዲስ አበባ ከተማ የትንሳዔን በዓል ምክንያት በማድረግ ማዕድ የማጋራት መርሃ ግብር እየተካሄደ ይገኛል

በአዲስ አበባ ከተማ የትንሳዔን በዓል ምክንያት በማድረግ በተለያዩ ክፍለ ከተሞች ማዕድ የማጋራት መርሃ ግብር እየተካሄደ ይገኛል።

በዚሁ መሠረት በተስፋ ብርሃን የምገባ ማዕከል በላይነህ ክንዴ ቅርንጫፍ የትንሳዔ በዓልን ምክንያት በማድረግ በዝቅተኛ የኑሮ ደረጃ ላይ ለሚገኙ ከ5 መቶ በላይ ነዋሪዎች ማዕድ የማጋራት መርሃ ግብር ተካሄዷል።

በመርሃ ግብሩ ላይ ተገኝተዉ ማዕድ ያጋሩት የአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር ምክትል ከንቲባ እና የኢንዱስትሪ ልማት ቢሮ ኃላፊ አቶ ጃንጥራር አባይ አዲስ አበባ በቀን ቢያንስ አንድ ጊዜ እንኳን መመገብ የማይችሉ ነዋሪዎቿን ባሏት 28 የምገባ ማዕከላት እየመገበች ስለመሆኗ አንስተዋል።

ከግሉ ባለሃብት ጋር በመተባበር የሚደረጉ መሰል ስራዎች የነዋሪዎችን የኑሮ ጫና በማቅለል ረገድ ያላቸው ሚና የጎላ መሆኑን በማንሳትም አቶ በላይነህ ክንዴ እና ፋውንዴሽናቸውን አመስግነዋል።

ጧሪ ደጋፊ የሌላቸው፣ በዝቅተኛ የኑሮ ደረጃ ላይ የሚገኙና የሃገር ባለውለታዎች በሰው ተኮር ተግባራት እየተደገፉ ስለመሆናቸው ያነሱት የቂርቆስ ክፍለ ከተማ ስራ አስፈፃሚ ምስክር ነጋሽ (ዶ/ር) በበኩላቸው፣ በዓላትን ከእነኚህ ነዋሪዎች ጋር የማሳለፍና ማዕድ የማጋራት ተግባር ባህል እየሆነ መምጣቱን ገልፀዋል። 

 የበላይነህ ክንዴ ፋውንዴሽን መስራችና ባለቤት አቶ በላይነህ ክንዴ በበኩላቸው፣ ካለህ ላይ ማካፈል ዕድል እንጂ ወጪ አይደለም ሲሉ ባለሃብቶች በዝቅተኛ የኑሮ ደረጃ ላይ የሚገኙ ዜጎችን ሊደግፉ እንደሚገባ አንስተዋል።


Comments

ምንም አልተገኘም.

አስተያየቶችዎን ይተዉት.