በመዲናችን አዲስ አበባ እውን እየሆኑ ባሉ ትላል...

image description
- ውስጥ Current Affairs    0

በመዲናችን አዲስ አበባ እውን እየሆኑ ባሉ ትላልቅ ፕሮጀክቶች 24/7 ያለእረፍት የበዓልን ቀን ጭምር በስራ ላይ ካሉ የአቃቂ ኢንዱስትሪ ክለሳተር ባለሙያዎች እና ሠራተኞች ጋር በመሆን ማዕድ በመቋደስ የትንሳዔ በዓልን አብረን አክብረናል።

መስራት ያስከብራል ድህነት ያዋርዳል ፣ በዓላችን ሙሉ የሚሆነው ሰርተን ስንበለፅግ ነው ብላችሁ ቀን ከሌሊት ሳትሉ ዛሬም ስራ ላይ የምታሳልፉ  ሁሉ እንኳን አደረሳችሁ ማለት እወዳለሁ።
 በዓሉን በጋራ ሆነን ማዕድ ስንቋደስ ለህዝባችሁ እንዲሁም ለከተማችሁ እድገት የምታደርጉትን አስተዋፅኦ እንዲሁም ድካማችሁ እውቅና እንዲሆንና በርቱ ለማለት ነው ።
 
መልካም የትንሳዔ በዓል 
 
ፈጣሪ ኢትዮጵያን እና ህዝቦችዋን ይባርክ!

ከንቲባ አዳነች አቤቤ


Comments

ምንም አልተገኘም.

አስተያየቶችዎን ይተዉት.