ለከተማዋ እፎይታን የሰጡት ዘመናዊ የመኪና ማቆሚ...

image description
- ውስጥ Current Affairs    0

ለከተማዋ እፎይታን የሰጡት ዘመናዊ የመኪና ማቆሚያዎች

በአዲስ አበባ ከተማ ከዚህ ቀደም በቂ የመኪና ማቆሚያ ስፍራ ባለመኖሩ በከተማዋ የሚንቀሳቀሱ ተሽከርካሪዎች በመንገድ ላይ ለረጅም ጊዜ በመቆም በትራፊክ ፍሰቱ ላይ ከፍተኛ መስተጓጎል ሲፍጠሩ እንደነበር አይዘነጋም፡፡

የአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር ችግሩን ከምንጩ ለመፍታት አዳዲስና በቴክኖሎጂ የታገዙ ዘመናዊ  የመኪና ማቆሚያ ተርሚናሎችን በመገንባት በከተማዋ የሚስተዋለውን የትራፊክ መጨናነቅ ከመቀነስ ባሻገር ለመዲናዋም ዘመናዊ ገጽታን እያላበሳት ይገኛል፡፡ 

አሁን ላይ በከተማዋ የተገነቡ የመኪና ማቆሚያዎች ዝናብና ፀሀይን የሚከላከሉ፣ ማረፊያ ስፍራ ያላቸው እና የደህንነት  ካሜራ የተገጠመላቸው በመሆኑ ከዚህ ቀድም ይደርስ የነበረውን  እንግልት ማስቀረት ተችሏል፡፡ 

በተጨማሪም ለተጠቃሚው እፎይታን ያላበሱ እነዚህ ዘመናዊ የመኪና ማቆምያዎች የትራፊክ መጨናነቅን በመቀነስ ፣ የትራንስፖርት ፍሰትን በማሳለጥ ፣ የትራፊክ አደጋን እንዲቀንስና የመኪና  ስርቆትን በመከላከል  የጊዜና የነዳጅ ብክነትን  በመቅረፍ ምርታማነት እንዲያድግ አስችለዋል፡፡ 

በቀጣይም የአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር የትራፊክ መጨናነቅን በከፍተኛ ደረጃ የሚያቃልሉና የትራንስፖርት ፍሰቱን የሚያሳልጡ ተጨማሪ አዳዲስ ዘመናዊ የመኪና ማቆሚያዎችን በመገንባት መዲናዋን ስማርት ሲቲ ለማድረግ የሚደረገውን ጥረት ይቀጥላል፡፡


Comments

ምንም አልተገኘም.

አስተያየቶችዎን ይተዉት.